ሲዳማ ቡና ከ ወላይታ ድቻ | ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

ሲዳማ ቡና1-0ወላይታ ድቻ

79′ አዲስ ግደይ


ተጠናቀቀ!

ጨዋታው በሲዳማ ቡና አሸናፊነት ተጠናቀቀ፡፡ ሲዳ በድቻ ላይ ያለውን የበላይነት ሲያከብር ዘንድሮ በሜዳው ያለውን 100% ሪኮርድም አስጠብቋል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ – 4 ደቂቃ

ቢጫ ካርድ

88′ ዳግም በቀለ አዲስ ግደይ ላይ በሰራው  ጥፋት ቢጫ ካርድ ተመልክቷል፡፡ በሁኔታውም ለአለም ብርሃኑ አላስፈላጊ ድርጊት በመፈፀሙ ቢጫ ተመልክቷል፡፡

84′ ዳግም በቀለ ከማዕዘን የተሻማውን ኳስ በግንባሩ ገጭቶ ለጥቂት ወጣበት፡፡ የሚያስቆጭ አጋጣሚ !

የተጫዋቸ ለውጥ – ሲዳማ ቡና

81′ በረከት አዲሱ ወጥቶ ሙጃይድ  መሃመድ ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ወላይታ ድቻ 

አናጋው ባደግ ወጥቶ አብዱልሰመድ አሊ ገብቷል፡፡

ጎልልል!!! ሲዳማ ቡና

79′ አዲስ ግደይ ከኤሪክ ሙራንዳ የተሻገረለትን ኳስ በግንባሩ ገጭቶ ወደ ግብነት በመቀየር ሲዳማን መሪ አድርጓል፡፡

77′ በዛብህ መለዮ ከርቀት በግራ እግሩ መሬት ለመሬት አክርሮ የመታው ኳስ ለጥቂት ወጣ፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ወላይታ ድቻ 

71′ ቴዎድሮስ መንገሻ ወጥሆ ዳግም በቀለ ገብቷል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ሲዳማ ቡና

71′ አንተነህ ተስፋዬ በጉዳት ወጥቶ ላኪም ሳኒ ገብቷል፡፡

65′ በድጋሚ ከመስመር የተሻገረውን ኳስ ኤሪክ ሙራዳ በግንባሩ ገጭቶ የግቡ አግዳሚ መልሶበታል፡፡ ሲዳማ ቡና ጫና ፈጥሮ በማጥቃት ላይ ይገኛል፡፡

63′ ከግራ መስመር ወሰኑ ማዜ ያሻማውን ኳስ አዲስ ግደይ በግንባሩ ገጭቶ የግቡን አግዳሚ ታኮ ወጥቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ወላይታ ድቻ  

60′ አማኑኤል ተሾመ ወጥቶ መሳይ አጪሶ ገብቷል፡፡

53′ አናጋው ባደግ ከግራ መስመር ያሻገረውን ኳስ በዛብህ መለዮ አገባው ሲባል በግቡ አናት ሰደደው፡፡ የሚያስቆጭ አጋጣሚ!

የተጫዋች ለውጥ – ሲዳማ
46′ ግሩም አሰፋ ወጥቶ ኤሪክ ሙራንዳ ገብቷል፡፡


ተጀመረ!
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡


እረፍት
የጨዋታው የመጀመርያ አጋማሽ ያለ ግብ ተጠናቋል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ – 1 ደቂቃ

33′ ቴዎድሮስ መንገሻ ከአላዛር ፋሲካ በግሩም ሁኔታ የተሻገረለትን ግልፅ የጎል አጋጣሚ አመከነ፡፡

ቢጫ ካርድ
26′ አዲስ ግደይ ሆን ብሎ ፍፁም ቅጣት ምት ክልል ውስጥ ወድቋል ተብሎ ቢጫ ካርድ ተመልክቷል:: አበበ ጥላሁንም የዳኛን ውሳኔ በመቃወም ቢጫ ካርድተመልክቷል፡፡

19′ ጨዋታው የመጀመሪያ አምስት ደቂቃ ከነበረው ፍጥነት ቀዝቀዝ ያለ ተመጣጣኝ የታከለበት እንቅስቃሴ  እየተመለከትን ነው፡፡
5′ በፈጣን እንቅስቃሴ ሲዳማ ቡና በተደጋጋሚ ወደ ጎል በመቅረብ ተጭኖ ለመጫወት ጥረት እያደረገ ነው፡፡

ተጀመረ!
ጨዋታው በወላይታ ድቻ አማካኝነት ተጀመረ

09:55 ታላቁን የደቡብ ደርቢ እንደ ወትሮ ሁሉ ለመከታተል በሺህ የሚቆጠር የስፖርት ቤተሰብ በስታድየሙ ታድሟል፡፡

09:50 ሁለቱም ቡድኖች ልምምዳቸውን አጠናቀው ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል


የሲዳማ ቡና አሰላለፍ

24 ለአለም ብርሃኑ

12 ግሩም አሰፋ – 4 አንተነህ ተስፋዬ – 21 አበበ ጥላሁን – 22 ወሰኑ ማዜ

8 ትርታዬ ደመቀ – 20 ሙሉአለም መስፍን – 5 ፍፁም ተፈሪ – 32 ሰንደይ ሙቱኩ – 14 አዲስ ግደይ

9 በረከት አዲሱ

 ተጠባባቂዎች

1 ፍቅሩ ወዴሳ

25 ክፍሌ ኪአ

23 ሙጃኢድ መሀመድ

19 አዲስ አለም ደበበ

11 ጸጋዬ ባልቻ

27 ላኪ ሰኒ

13 ኤሪክ ሙራንዳ

ወላይታ ድቻ

1 ወንድወሰን ገረመው

6 ተክሉ ታፈሰ – 27 ሙባረክ ሽኩር – 3 ፈቱዲን ጀማል

9 ያሬድ ዳዊት – 8 አማኑኤል ተሾመ – 17 በዛብህ መለዮ – 29 ወንድማገኝ በለጠ – 7 አናጋው ባደግ

19 አላዘር ፋሲካ – 16 ቴዎድሮስ መንገሻ

ተጠባባቂዎች

12 ወንድወሰን አሸናፊ 

3 ቶማስ ስምረቱ 

5 ዳግም ንጉሴ 

20 አብዱልሰመድ አሊ

21 መሳይ አጪሶ

23 ጸጋዬ በርሃኑ 

13 ዳግም በቀለ

Leave a Reply