ፋሲል ከተማ2-1ቅዱስ ጊዮርጊስ
12′ ሳላዲን ሰኢድ | 45′ አብዱራህማን ሙባረክ 88′ ኤዶም ሆሶሮቪ
ተጠናቀቀ !!!!
ጨዋታው በፋሲል ከተማ አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ አዲስ አዳጊው ክለብ ፋሲል ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች በማሸነፍ አጀማመሩን አሳምሯል፡፡
ተጨማሪ ደቂቃ – 3
ጎልልል – ፋሲል ከተማ
88′ ኤዶም ሆሶሮ የተገኘውን የፍጹም ቅጣት ምት ወደ ግብነት ቀይሮታል፡፡
ፍጹም ቅጣት ምት!
87′ ኤዶም በፍጹም ቅጣት ምት ክልል ውስጥ ተጠልፎ በመውደቁ የፍጹም ቅጣት ምት ለፋሲል ተሰጥቷል፡፡
ቢጫ ካርድ
83′ አምበሉ ታደለ ባይሳ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
79′ አብዱልከሪም ኒኪማ ወጥቶ አቡበከር ሳኒ ገብቷል፡፡
ተጫዋች ለውጥ – ፋሲል ከተማ
70′ ሰለሞን ገብረመድህን ወጥቶ ኤፍሬም አለሙ ገብቷል፡፡
67′ ይስሃቅ መኩርያ ሳጥን ውስጥ ያገኘውን ኳስ ሞክሮ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡
65′ ተስፋዬ አለባቸው ከቅጣት ምት የሞከረውን ኳስ ዮሃንስ አድኖበታል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
54′ ምንያህል ተሾመ ወጥቶ ተስፋዬ አለባቸው ገብቷል
49′ አብዱራህማን በአንድ ሁለት ቅብብል ወደ ጊዮርጊስ የግብ ክልል በመግባት የሞከረው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡
ተጀመረ
2ኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡
እረፍት
የመጀመርያው አጋማሽ በአቻ ውጤተት ተጠናቋል፡፡
ጎልልል!!!! ፋሲል ከተማ
45′ ወደ ግብ የተላከውን ኳስ ተከላካዮች ሲመልሱት አብዱራህማን አግኝቶ ፋሲልን አቻ አድርጓል
43′ ሰኢድ ሀሰን ከርቀት የሞከረው ኳስ ኢላማውን ሳይጠብቅ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡
38′ ከቅጣት ምት የተሻገረውን ኳስ ናትናኤል ሞክሮ የቡድን አጋሩ አበባው መልሶበታል፡፡
36′ ሳላዲን ሰኢድ ከመሃል ሜዳ እየገፋ የመጣውን ኳስ ወደ ግብ ሞክሮ ኢላማውን ሳይጠብቅ ቀርቷል፡፡
34′ አብዱራህማን ወደ ግብ የመታውን ኳስ ሮበርት በአስደናቂ ሁኔታ አድኖበታል፡፡
31′ ሳላዲን ከ አዳነ የተሻገረለትን ኳስ ወደ ግብ ሞክሮ ለጥቂት ወጥቶበታል፡፡
29′ አብዱራህማን ሙባረክ የመታውን ኳስ ኦዶንካራ አድኖታል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ፋሲል ከተማ
26′ ኤርሚያስ ኃይሉ በጉዳት ወጥቶ ናትናኤል ጋንጂላ ገብቷል፡፡
ቢጫ ካርድ
22′ ምንተስኖት አዳነ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡
ጎልልል!!! ቅዱስ ጊዮርጊስ
12′ ሳላዲን ሰኢድ የተከላካዮች እና የግብ ጠባቂውን አለመግባባት ተጠቅሞ ቅዱስ ጊዮርጊስን መሪ አድርጓል፡፡
ተጀመረ!
ጨዋታው ተጀምሯል፡፡
የፋሲል ከተማ አሰላለፍ
93 ዮሃንስ ሻኩር
5 ታደለ ባይሳ – 13 ሰኢድ ሁሴን – 21 አምሳሉ ጥላሁን – 16 ያሬድ ባየህ
17 ይስሃቅ መኩሪያ – 26 ሄኖክ ገምተሳ – 27 ሰለሞን ገ/መድህን – 99 ኤርምያስ ሃይሉ
18 አቡዱርሀማን ሙባረክ – 9 ኤዶም ሆሮሶውቪ
ቅዱስ ጊዮርጊስ አሰላለፍ
30 ሮበርት ኦዶንካራ
4 አበባዉ ቡጣቆ – 5 አይዛክ ኢሴንዴ – 23 ምንተስኖት አዳነ – 2 ፍሬዘር ካሳ
14 ምንያህል ተሾመ – 26 ናትናኤል ዘለቀ – 27 አብዱልከሪም ነኪማ – 16 በሃይሉአሰፋ
7 ሳላዲን ሰኢድ – 19 አዳነ ግርማ