ሙሉዓለም ጥላሁን ለመከላከያ ለመጫወት ተስማማ

በሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽን ዋንጫ ኢትዮጵያ ቡና በቲፒ ማዜንቤ 3-1 በተረታበት ጨዋታ ባሳየው ያልተገባ ባህርይ ከደጋፊዎችና አሰልጣኝ ስታፉ ጋር እሰጥ አገባ ውስጥ ገብቶ የነበረው እና ላልተወሰነ ጊዜ ታግዶ የቆየው አጥቂው ሙሉአለም ጥላሁን ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ያለውን ውል አፍርሶ ለመከላከያ መፈረሙን ፕላኔት ስፖርት ዘግቧል፡፡ 

ሙሉአለም ውሉን ማፍረሱን ተከትሎ የቀድሞ ክለቡ ኢትዮጵያ መድንን ጨምሮ በበርካታ ክለቦች ቢፈለግም መከላከያን ተቀላቅሏል፡፡ ከ2003 ጀምሮ በኢትዮጵያ ቡና የቆየው ሙሉአለም አምና ኮንትራቱን ሲያራዝም ለፊርማ ከተቀበለው ውስጥ ግማሹን መልሶ ከክለቡ መልቀቅያ መውሰዱ ሲገለፅ በውድድር ዘመኑ አጋማሽ በይፋ የመከላከያ ተጫዋች ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ መከላከያ ለዝውውሩ 250,000 ብር ወጪ ማድረጉም ተነግሯል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ