ዋልያዎቹ መቼ ዝግጅት እንደሚጀምሩ አልታወቀም

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለወትሮው ለትልልቅ ውድድሮች ቢያንስ አንድ ወር ዝግጀት የማድረግ ልማድ ቢኖረውም በ2014 መጀመርያ በሀገር ውስጥ ሊግ ውስጥ በሚጫወቱ ተጫዋቾች ብቻ በሚዋቀር ስብስብ ለሚደረገው ውድድር (ቻን) እስካሁን ዝግጅት አልጀመረም፡፡

ውድድሩ ሊጀመር የ23 ቀናት እድሜ የቀሩት ቢሆንም ኢትዮጵያ እስካሁን ተጫዋቾቿን አላሳወቀችም (በምድባችን የምትገኘው ጋና ከወዲሁ 23 ተጫዋቿን አሳውቃለች)፡፡ አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው በመጪው ሳምንት ሰኞ ዝግጅት ለመጀመር ጥያቄ ቢያቀርቡም የሊጉ ውድድር እንዳይቋረጥ በሚል በፌዴሬሽኑ ውድቅ ተደርጎባቸዋል፡፡

ኢትዮጵያ በቻን ምድብ ሦስት ከኮንጎ ሪፐብሊክ (ብራዛቪል)፣ ሊቢያ እና ጋና ጋር መደልደሏ ይታወሳል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ