ብሄራዊ ሊጉ የሚጀመርበት ቀን በድጋሚ ተራዘመ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሊግ የ2009 የውድድር ዘመን የሚጀመርበት ቀን ለ3ኛ ጊዜ ተራዝሟል፡፡

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የውድድሩ ተሳታፊ ክለቦች መክፈል የሚጠበቅባቸውን የዳኞች እና ታዛቢዎች ክፍያ ባለማጠናቀቃቸው ሊጉ የሚጀመርበት ቀን ወደ ታህሳስ 2 ቢሸጋገርም አሁንም ክለቦች ክፍያ ባለማጠናቀቃቸው በድጋሚ ለታህሳስ 8 እንዲሸጋገር ተደርጓል፡፡ ፌዴሬሽኑ ባደረገው ውይይት ውድድሩ ከዚህ በኋላ እንደማይራዘምና ክፍያውን ባጠናቀቁ ክለቦች መካከል ለመጀመር እንዳሰበ ታውቋል፡፡

በውድድሩ ላይ ከሚሳተፉ ክለቦች መካከል አንዳንዶቹ መፍረሳቸው የተነገረ ሲሆን የመሳተፍ አለመሳተፍ ውሳኔዎችን እስካሁን ያላሳወቁ ክለቦች መኖራቸውም ታውቋል፡፡ በፈረሱ ክለቦች ምትክም አዳዲስ ክለቦች እንዲካተቱ ለማድረግ እየተሞከረ እንደሆነ ተሰምቷል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *