በፕሪሚየር ሊግ ክለቦች መካከል ብቻ እየተካሄደ የሚገኘው የ2007 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ዋንጫ (ጥሎ ማለፍ) ውድድር የመጀመርያ ዙር ትላንት በተደረጉ ጨዋታዎች ተጠናቋል፡፡

ትላንት በተደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ወላይታ ድቻ እና ኤሌክትሪክ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈው ወደ ሩብ ፍፃሜው ሲቀላቀሉ ባለፈው ቅዳሜ ሀሙስ እለት ተጋጣሚዎቻቸውን ያሸነፉት ሀዋሳ ከነማ ፣ ሲዳማ ቡና ፣ መከላከያ እና አርባምንጭ ከነማ እንዲሁም የመጀመርያውን ዙር ሳይጫወቱ ወደ ሩብ ፍፃሜው በቀጥታ የተቀላቀሉት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና ሌሎቹ ሩብ ፍፃሜውን የተቀላቀሉ ክለቦች ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የቀጣይ ጨዋታዎችን ቀን ይፋ አላደረገም፡፡

 

የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ አርባምንጭ ከነማ

ሲዳማ ቡና ከ መከላከያ

ኤሌክትሪክ ከ ወላይታ ድቻ

ኢትዮጵያ ቡና ከ ሀዋሳ ከነማ

 

የ1ኛው ዙር ውጤቶች

23/05/2007 ሙገር ሲሚንቶ 1-1 (3-4) አርባምንጭ ከነማ

23/05/2007 ሲዳማ ቡና 3-0 ወልድያ

28/05/2007 ዳሽን ቢራ 0-2 መከላከያ

30/05/2007 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1-3 ኤሌክትሪክ

30/05/2007 አዳማ ከነማ 1-2 ወላይታ ድቻ

28/05/2007 ሀዋሳ ከነማ 2-2 (3-2) ደደቢት

ያጋሩ