ኢትዮጵያ ቡና ከ ሲዳማ ቡና | ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

ኢትዮጵያ ቡና2-1ሲዳማ ቡና

10′ ሳሙኤል ሳኑሚ (ፍ.ቅ.ም.)፣ 23′ ያቡን ዊልያም | 54′ ፍፁም ተፈሪ


ተጠናቀቀ!!!

ጨዋታው በኢትዮጵያ ቡና 2-1 አሸናፊነት ተጠናቋል። ክለቡም የ2009 የውድድር ዓመት የመጀመሪያ 3 ነጥቡን ማሳካት ችሏል።90+3′ አህመድ ረሺድ እና ኤፍሬም የወንድወሰን ሰዓት በማባከን ቢጫ ካርድ አይተዋል።


90+1′ የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ ቡና

ኤልያስ ማሞ ወጥቶ ወንድይፍራው ጌታሁን ገብቷል።


90′ ተጨማሪ ሰዓት – 4 ደቂቃ


88′ ፍፁም ተፈሪ የዳኛን ውሳኔ በመቃወም የቢጫ ካርድ ተመልክቷል።


85′ ውጤቱን አብዝተው የሚፈልጉት የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ቡድናቸው የውድድር ዓመቱን የመጀመሪያ 3 ነጥብ እንዲያሳካ ከፍተኛ ድጋፍ እየሰጡ ይገኛሉ።


82′ ኤልያስ ማሞ ከሳጥኑ ውጪ የመታውን ኳስ ለዓለም አውጥቶታል።


81′ የተጫዋች ለውጥ – ሲዳማ ቡና

ኤሪክ ሙራንዳ ወጥቶ ሙጀሢድ መሐመድ ገብቷል።


77′ አብዱልከሪም ለአማኑኤል በጥሩ ሁኔታ የሰጠውን ኳስ አማኑኤል ወደግብ መለወጥ አልቻለም።


76′ አብዱልከሪም መሐመድ ከርቀት የመታውን ኳስ ለዓለም በቀላሉ ይዞታል።


73′ የተጫዋች ለውጥ – ሲዳማ ቡና

ትርታዬ ደመቀ ወጥቶ ላኪ ሳኒ ገብቷል።


72′ አማኑኤል ዮሐንስ ከኤልያስ የተቀበለውን ኳስ ከርቀት ሞክሮ ግብ ጠባቂው መልሶበታል።


70′ የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ ቡና

ሳሙኤል ሳኑሚ ወጥቶ ሳለአምላክ ተገኝ ገብቷል።


66′ ጋቶች ፓኖም ፊሽካ ከተነፋ በኀላ ኳስ በመምታቱ የማስጠንቀቂያ ካርድ አይቷል።


62′ የሲዳማ ቡና ግብ ጠባቂ ለዓለም ብርሃኑ በተደጋጋሚ እየሰራቸው ያሉ ስህተቶች ብድኑን ዋጋ ለማስከፈል የቀረቡ ናቸው።


60′ አህመድ ረሺድ በሳጥኑ ውስጥ ተጠልፌያለሁ ብሎ ቢወድቅም ዳኛው ፍፁም ቅጣት ምት ከልክለዋል።


55′ የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ ቡና

ሳዲቅ ሴቾ ወጥቶ እያሱ ታምሩ ገብቷል።


54′ ጎልልል!!! ሲዳማ

ፍፁም ተፈሪ ፀጋዬ ባልቻ ያሻማውን ኳስ ተቆጣጥሮ ወደግብ በመቀየር ልዩነቱን ማጥበብ ችሏል።


52′ ፀጋዬ ባልቻ ከርቀት የመታው ኳስ ወደውጪ ወጥቷል። ሲዳማ በሁለተኛው አጋማሽ ተጭኖ ለመጫወት እየሞከረ ይገኛል።


46′ ሁለተኛው የጨዋታ አጋማሽ ተጀምሯል።


የተጫዋች ለውጥ – ሲዳማ ቡና

አንተነህ ተስፋዬ ወጥቶ ፀጋዬ ባልቻ ገብቷል።


 

የመጀመሪያው አጋማሽ በኢትዮጵያ ቡና 2-0 መሪነት ተጠናቋል።


45′ ተጨማሪ ሰዓት – 2 ደቂቃ


36′ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች በስታዲየሙ የሜክሲኮ ማዕበል (Mexican Wave) ትዕይንት እያሳዩ ይገኛሉ።


33′ ሳኑሚ በአስደናቂ ሁኔታ ያቀበለውን ኳስ አማኑኤል ዮሐንስ ሞክሮ ግብ ጠባቂው አውጥቶታል።


31′ አበበ ጥላሁን ከሳጥኑ ጠርዝ ላይ የመታውን ቅጣት ምት ግብ ጠባቂው ሃሪስተን ይዞታል።


28′ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች በውጤት ማጣት ውስጥ የነበረው ቡድናቸው በሁለት ግብ ልዩነት መምራት መቻሉን ተከትሎ ደማቅ የሆነ ድባብ በስታዲየሙ ፈጥረዋል።


25′ ኤሪክ ሙራንዳ በአህመድ ረሺድ ላይ በሰራው ጥፋት ምክኒያት የመጀመሪያውን ቢጫ ካርድ ተመልክቷል።


23′ ጎልልል!!! ኢትዮጵያ ቡና!!!

ያቡን ዊልያም ከሳኑሚ በጥሩ ሁኔታ የተሻገረለትን ኳስ በመጠቀም የግብ ልዩነቱን ማስፋት ችሏል።


15′ ሳሙኤል ሳኑሚ ከግብ ጠባቂው ጋር ተገናኝተው የሞከረው ኳስ ተይዞበታል።


10′ ጎልልል!!! ኢትዮጵያ ቡና

ሳሙኤል ሳኑሚ ፍፁም ቅጣት ምቱን በመጠቀም ኢትዮጵያ ቡናን መሪ አድርጓል።


9′ አህመድ ረሽድ በሳጥኑ ውስጥ በሳውሬል ኦልሪሽ በመጠለፉ ፍፁም ቅጣት ምት ለኢትዮጵያ ቡና ተሰጥቷል።


4′ አህመድ ረሺድ ጉዳት አጋጥሞት የህክምና እርዳታ ካገኘ በኀላ ወደሜዳ ተመልሷል።


1′ ጨዋታው በኢትዮጵያ ቡና አማካኝነት ተጀምሯል።ከ1977 እስከ 1981 ድረስ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለተጫወተው እና በዚህ ሳምንት ከዚህ ዓለም በሞት ለተለየው ዘላለም ተሾመ የ1 ደቂቃ የህሊና ፀሎት ተደርጓል።


የሲዳማ ቡና አሰላለፍ

24. ለአለም ብርሃኑ

15. ሳውሬል ኦልርሽ– 4. አንተነህ ተስፋዬ – 21. አበበ ጥላሁን — 32. ሳንደይ ሙቱኩ

22. ወሰኑ ማዜ– 20. ሙሉአለም መስፍን — 8. ትርታዬ ደመቀ — 5. ፍፁም ተፈሪ

14. አዲስ ግደይ — 13. ኤሪክ ሙራንዳ

ተጠባባቂዎች

1. ፍቅሩ ወዴሳ

23. ሙጃኢድ መሀመድ

12. ግሩም አሰፋ

19. አዲስአለም ደበበ

11. ጸጋዬ ባልቻ

27. ላኪ ሰኒ

10. አብይ በየነ


የኢትዮጵያ ቡና አሰላለፍ
99. ሀሪስን ሄሱ

15. አብዱልከሪም መሀመድ — 16. ኤፍሬም ወንድወሰን — 4. ኤኮ ፌቨር — 13. አህመድ ረሽድ

9. ኤልያስ ማሞ — 25. ጋቶች ፓኖም– 8. አማኑኤል ዮሐንስ

7. ሣዲቅ ሤቾ — 28. ያቡን ዊልያም — 11. ሳሙኤል ሳኑሚ
ተጠባባቂዎች

50. ጆቤድ ኡመድ

18. ሣለአምላክ ተገኝ

14. እያሱ ታምሩ

5. ወንድይፍራው ጌታሁን

27. ዮሴፍ ዳሙዬ

17. አብዱልከሪም ሀሰን

20. እሱባለው ጌታሁን

Leave a Reply