ሀዋሳ ከተማ በተጫዋቾቹ ላይ ቅጣት አስተላለፈ

ባሳለፍነው እሁድ በሀዋሳ ከተማ ስታድየም ሀዋሳ ከተማ ከ መከላከያ ጋር ሁለት አቻ በተለያዩበት የፕሪምየር ሊግ 5ኛ ሳምንት ጨዋታ 3 ተጫዋቾች ከሀዋሳ ፣ 1 ተጫዋች ከመከላከያ በቀይ ካርድ ከሜዳ መሰናበታቸው ይታወሳል፡፡

ክለቡ ከጨዋታው በኃላ ባደረገው ግምገማ ያልተገባ ባህሪ ያሳዩት ተጫዋቾቹን መጠኑ በይፋ ያልተገለጸ ገንዘብ ቀጥቷል፡፡ በዲሲፕሊን ጥሰቱ ምክንያት ፌዴሬሽኑ የሚያስተላልፈውን የገንዘብ ቅጣት ተጫዋቾቹ እንዲከፍሉ ሲወሰን ዳግም ተመሳሳይ ግድፈት እንዳይፈጽሙም ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል፡፡

ሀዋሳ ከተማ የእሁዱን ጨዋታ የዲሲፕሊን ግድፈት ተከትሎ አንበሎችንም ቀይሯል፡፡ ግርማ በቀለን ተክቶ የግራ ተከላካዩ ደስታ ዮሀንስ የክለቡ አዲስ አምበል ተደርጎ ሲመረጥ በእሁዱ ጨዋታ በተጠበባቂ ወንበር በፈጠረው ፀብ በቀይ ካርድ በተሰናበተው ሁለተኛው አምበል አዲስአለም ተስፋዬ ምትክ አዲሱ ፈራሚ ፍሬው ሰለሞን 2ኛ አምበል ሆኗል፡፡  አማካዩ ኃይማኖት ወርቁ ደግሞ በዳንኤል ደርቤ ምትክ 3ኛ አምበል ሆኗል፡፡

ሀዋሳ ከተማ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 6ኛ ሳምንት ወደ ጎንደር አቅንቶ ፋሲል ከተማን ይገጥማል፡፡

4 Comments

  1. hahaha mulum huno aychilene ahunma techawetnbet facil ketema

  2. ያልተገባ ባህሪይንና ድርጊትን ልመቆጠር አግባብነት ያለው ውሳኔ ነው። ቢሆንም ተጫዋቾቹ ላይ የተጣለው/የሚጣለው ቅጣት እንደጥፋታቸውና እንደጥፋቱ መንስኤ መለያየት አለበት(ቀይ ስላዩ ብቻ እንዳይሆን)።

  3. personally i do not accept what the club take the action on the players in some extent they deserve their hands but the main key players are the main referees and the side line referees so that ETHIOPIAN FOOTBALL FEDERATION take the action on them unless & other wise we dont expect fair decision. unreasonably he gave three red card except Gadissa Meberates red cared.

Leave a Reply