ፍቅሩ በመጀመሪያ ጨዋታው ለዊትስ ግብ አስቆጠረ
ኢትዮጵያዊው አጥቂ ፍቅሩ ተፈራ በደቡብ አፍሪካ አብሳ ፕሪምየርሺፕ ለአዲሱ ክለቡ ቤደቬስት ዊትስ ማክሰኞ ምሽት በተደረገ ጨዋታ ማርቲዝበርግ ዩናይትድ ላይ ግብ አስቆጠረ፡፡
ፍቅሩ በመጀመሪያው ጨዋታው ለዊትስ ግብ ማስቆጠሩ አስገራሚ ሆኗል፡፡ ማርቲዝበርግ ዩናይትዶች በጨዋታው መምራት ቢችልም ዊትስ 2 ግቦችን አስቆጥሮ 2ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፎ ወጥቷል፡፡ ለዊትስ 2ኛውን ግብ ኢትዮጵያዊው ፍቅሩ ተፈራ የመጀመሪያው ግማሽ ሊጠናቀቅ በተቃረበበት ጊዜ በግምባር በመግጨት አስቆጥሯል፡፡ ፍቅሩ ለአዲሱ ክለቡ 12 ቁጥር መለያ ተስጥቶታል፡፡
በ6 ወር ውል ቤድቬስት ዊትስ የተቀላቀለው ፍቅሩ በመጀመሪያው ጨዋታ ግብ ማስቆጠሩ አሰልጣኝ ጋቭን ሃንትን አስደስቷል፡፡ ዊትስ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ በ34 ነጥብ 3ኛ ነው፡፡ ከመሪው ካይዘር ቼፍስ ጋር የ12 ነጥብ ልዩነት አለ፡፡ በተያያዘ ዜና ሌላኛው አትዮጵያዊ አጥቂ ጌታነህ ከበደ የተጠባባቂ ወንበር ላይ መቀመጡን ቀጥሎበታል፡፡ ጌታነህ ለዊትስ ተስልፎ ለመጫወት ተስኖታል፡፡
ተዛማጅ ፅሁፎች
ቅድመ ዳሰሳ | የ25ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ጨዋታዎች
ሊጉ ለብሔራዊ ቡድን ዝግጅት እና ጨዋታዎች ከመቋረጡ በፊት የሚደረጉት የጨዋታ ሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ፍልሚያዎች እንዲህ ተዳሰዋል። አዲስ አበባ ከተማ ከ...
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ | 24ኛ ሳምንት ምርጥ 11
እንደ ሁልጊዜው ባሳለፍነው ሳምንት በተደረጉ ጨዋታዎች ላይ ጎልተው የወጡ ተጫዋቾችን ያካተተ ቡድን ሰርተናል። አሰላለፍ (4-3-2-1) ግብ ጠባቂ አቡበከር ኑራ -...
ብሔራዊ ቡድኑ ለ28 ተጫዋቾች ጥሪ አቅርቧል
የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ከቀናት በኋላ ማድረግ የሚጀምረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለተጫዋቾቹ ጥሪ አስተላልፏል። በ2023 በአይቮሪኮስት አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ...
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰላለፍ ታውቋል
10:00 ላይ ከናይጄሪያ አቻው ጋር ወሳኝ ጨዋታ የሚጠብቀው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰላለፍ ታውቋል። በሕንድ ለሚደረገው የሴቶች...
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 21ኛ ሳምንት ዓበይት ጉዳዮች (፫) – አሰልጣኞች ትኩረት
በሦስተኛው የሳምንቱ የዓበይት ጉዳይ ፅሁፋችን አሰልጣኞች ላይ ያተኮሩ ሀሳቦች ተዳሰውበታል። 👉 ፋሲል ተካልኝ እና አዳማ ተለያይተዋል በክረምቱ አዳማ ከተማን የተረከበው...
በሦስት ዳኞች ላይ ውሳኔ ተላልፏል
በወላይታ ድቻ እና በኢትዮጵያ ቡና ክስ ተመስርቶባቸው የነበሩ ዳኞች ከፕሪምየር ሊጉ ውድድር ተሸኝተዋል፡፡ በኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የ24ኛ ሳምንት ጨዋታ...