ደደቢት ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ | ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

ደደቢት2-0ኢትዮ ኤሌክትሪክ

59′ አስራት መገርሳ፣ 64′ ጌታነህ ከበደ


ጨዋታው በደደቢት 2-0 አሸናፊነት ተጠናቋል።


90′ ተጨማሪ ሰዐት – 3 ደቂቃ


84′ የተጫዋች ለውጥ – ደደቢት

ሺመክት ጉግሳ ወጥቶ ያሬድ ብርሃኑ ገብቷል።


80′ የተጫዋች ለውጥ – ደደቢት

ጌታነህ ከበደ ወጥቶ ደስታ ደሙ ገብቷል።


75′ የተጫዋች ለውጥ – ኤሌክትሪክ

ዋለልኝ ገብሬ ወጥቶ በሀይሉ ተሻገር ገብቷል።

ብሩክ አየለ ወጥቶ አቤል አክሊሉገብቷል።


70′ ኤሌክትሪኮች ግብ ለማግኘት ጥረት እያደረጉ ቢሆንም ደደቢቶች በመልሶ ማጥቃት የተሻሉ ዕድሎች እየፈጠሩ ይገኛሉ።

 

 


64′ ጎል!!!

ጌታነህ ከበደ የአወት ገብረሚካኤልን ስህተት በመጠቀም በሊጉ 6ኛ ጎሉን አስቆጥሯል።


59′ ጎል!!!!

ጌታነህ ከበደ ከ30 ሜትር ርቀት አካባቢ የመታውን ቅጣት ምት ግብ ጠባቂው ሲመልሰው አስራት መገርሳ አግኝቶ በማስቆጠር ደደቢትን መሪ አድርጓል።


55′ ጌታነህ ከበደ ያገኘውን ኳስ ነፃ ሆኖ ለሚጠብቀው ዳዊት ፍቃዱ ማድረስ ባለመቻሉ አጋጣሚው ሊባክን ችሏል።


50′ ሙሉአለም ጥላሁን ሁለት ተጫዋቾችን በማለፍ የመታውን ኳስ ክሌመንት አሺቴይ መልሶታል።


46′ ሁለተኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል።የመጀመሪያው አጋማሽ ያለግብ አቻ ተጠናቋል። የደደቢቱ አምበል ስዩም ተስፋዬ ወደ ዳኞቹ በመሄድ ቅሬታውን እየገለፀ ይገኛል።


45+1′ አሸናፊ ሽብሩ ከርቀት የመታው ኳስ ወደውጪ ወጥቷል።


45′ ተጨማሪ ሰዐት – 2 ደቂቃ


40′ ሰለሞን ሀብቴ በደረሰበት ጉዳት ምክኒያት የህክምና ዕርዳታ እየተሰጠው ይገኛል።


32′ ኤሌክትሪኮች ያላቸውን የቁጥር ብልጫ ተጠቅመው ግብ ለማስቆጠር ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ።


28′ ፍፁም ገብረማርያም ከቅጣት ምት የሞከረው ኳስ ከግቡ አናት በላይ ወጥቷል።


21′ ሙሉአለም ጥላሁን ያገኘውን መልካም አጋጣሚ መጠቀም አልቻለም።


16′ ኢብራሂም ፎፋኖ ኳስ በእጁ ሊቆጣጠር በመሞከሩ የማስጠንቀቂያ ካርድ አይቷል።


12′ አይናለም ሀይሉ አለምነህ ግርማ ላይ ከኃላ በሁለት እግሩ በመጥለፍ አደገኛ ጥፋት በመፈፀሙ በቀጥታ ቀይ ከሜዳ ተወግዷል።


8′ ጌታነህ ከበደ የተላከለትን ኳስ ከማግኘቱ በፊት ግብ ጠባቂው ከቦታው በመልቀቅ አውጥቶበታል።


5′ ኤሌክትሪኮች ከማዕዘን ምት ያሻሙት ኳስ በእጅ ተነክቷል በሚል ፍፁም ቅጣት ምት እንዲሰጣቸው ቢጠይቁም ዳኛው በዝምታ አልፈዋል።


1′ ጨዋታው በደደቢት አማካኝነት ተጀምሯል።የደደቢት አሰላለፍ

33 ክሌመንት አሼቲ

7 ስዩም ተስፋዬ — 6 አይናለም ኃይለ –14 አክሊሉ አየነው — 16 ሰለሞን ሐብቴ

24 ካድር ኩሊባሊ — 4 አስራት መገርሳ — 8 ሳምሶን ጥላሁን — 19 ሽመክት ጉግሳ

9 ጌታነህ ከበደ — 17 ዳዊት ፍቃዱ


ተጠባባቂዎች

22 ታሪክ ጌትነት

11 አቤል ያለው

15 ደስታ ደሙ

18 አቤል እንዳለ

2 ሔኖክ መርሻ

27 እያሱ ተስፋዬ

99. ያሬድ ብርሀኑ


ኤሌክትሪክ አሰላለፍ

22 ሱሊማን አቡ

11 አወት ገ/ሚካኤል — 5 አዲስ ነጋሽ (አምበል) –15 ተስፋዬ መላኩ —  7 አለምነህ ግርማ

23 አሸናፊ ሽብሩ — 24 ዋለልኝ ገብሬ — 9 ብሩክ አየለ

16 ፍፁም ገ/ማርያም — 18 ሙሉአለም ጥላሁን —  4  ኢብራሂም ፎፋኖ

ተጠባባቂዎች

1 ኦኛ ኦሜኛ

19 ደረጄ ሀይሉ

14 ስንታየው ሠለሞን

8 በሀይሉ ተሻገር

17  አብዱልሐኪም ሱልጣን

12 ትዕዛዙ መንግስቱ

2 አቤል አክሊሉ


Leave a Reply