አዳማ ከተማ ከ ወልድያ | ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

አዳማ ከተማ1-0ወልድያ

6′ ሲሳይ ቶሊ


ተጠናቀቀ!!

ጨዋታው በአዳማ አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

90+3′ ብሩክ ቃልቦሬ የሞከረው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል

90′ ተጨማሪ አራት ደቂቃ ተጨምሯል

90′ ፋሲካ አስፋው አስከነ ህመሙ ወደ ሜዳ ተመልሶ ገብቷል፡፡

89′ ፋሲካ አስፋው የትከሻ ጉዳት አጋጥሞት ከሜዳ ወጥቷል፡፡

73′ ብሩክ ቃልቦሬ የሞከረው ኳስ ለጥቂት የግቡን ቋሚ ታካ ወጥታለች፡፡
66′ የተጫዋች ለውጥ – ወልዲያ

ጫላ ድሪባ ወጥቶ በድሩ ኑርሁሴን እንዲሁም ያሬድ ሀሰን ወጥቶ ሙሉነህ ጌታሁን ገብተዋል፡፡

ተጫዋች ለውጥ – አዳማ

62′ ሚካኤል ጆርጅ ወጥቶ ጥላሁን ወልዴ እንዲሁም አዲስ ህንፃ ወጥቶ ሄኖክ ካሳሁን ገብተዋል፡፡

51′ ታፈሰ ተስፋዬ በቀኝ በኩል ሰብሮ በመግባት ያደረገውን ሞከራ ቤሌንጌ አድኖበታል፡፡

49′ አንዱአለም ንጉሴ የሞኞትን ስህተት ተጠቅሞ የሞከረውን ኳስ ጃኮብ በቀላሉ ይዞበታል፡፡

ተጀመረ!!

ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡

እረፍት!!

የመጀመርያው አጋማሽ ያለ ግብ ተጠናቋል፡፡

45+1′ ከ30 ሜትር ርቀት የተገኘውን ቅጣት ምት አንዱአለም ንጉሴ በቀጥታ ሞክሮ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡
42′ ከማእዘን የተሻማውን ኳስ አንዱአለም ንጉሴ በግንባሩ ገጭቶ ቢሞክርም ሱሌይማን ከመስመር ላይ አውጥቷታል፡፡
35′ ሚካኤል ጆርጅ ያሸለኮለትን ኳስ ታፈሰ ከግብ ጠባቂው ጋር አንድ ለአንድ ተገናኝቶ አምክኗል፡፡

31′ ሲሳይ ከግራ መስመር ወደ ግብ ያሻገረውን ኳስ ታፈሰ ሚዛኑን መጠበቅ ባለመቻሉ የተገኘውን ወርቃማ እድል ሳይጠቀም ቀርቷል፡፡

27′ ሱሌይማን መሀመድ የግሉን ጥረት ተጠቅሞ በግራ መስመር አቅጣጫ የወልዲያ ተከላካዮችን አለፎ ሳጥን ውስጥ ከገባ በኃላ ማቀበል ሲገባው ወደ ግብ በቀጥታ የሞከራት ኳስ ከግቡ አናት በላይ ወጥታለች፡፡
20′ ሀብታሙ ሸዋለም ከግብ ክልል ውጪ አክርሮ የመታው ኳስ ከግቡ አናት በላይ ወጥቷል፡፡

17′ አዳማ ከተማዎች ኳሱን ከወልዲያ በተሻለ ተቆጣጥረው ለመጫወት ጥረት እያደረጉ ይገኛል፡፡

12′ ፋሲካ አስፋው ከቀኝ መስመር ያሻማውን ኳስ ለጥቂት ታፈሰ ሳይደርስባት ቀርቷል፡፡

ጎልልል!! አዳማ ከተማ

6′ ሲሳይ ቶሊ ከሱሌይማን የተሻማለትን ኳስ ተቆጣጥሮ የወልዲያ ተከላካዮችን በማታለል አስቆጥሯል፡፡

5′ ሚካኤል ጆርጅ ከግብ ክልል ውጪ የመታው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

ተጀመረ!
ጨዋታው ተጀምሯል፡፡

አዳማ ከተማ አሰላለፍ
ጃኮብ ፔንዜ
ሲሳይ ቶሊ – ተስፋዬ በቀለ –  ምኞት ደበበ – ሱሌይማን መሀመድ
ብሩክ ቃልቦሬ – ፋሲካ አስፋው -አዲስ ህንፃ
ሚካኤል ጆርጅ – ታፈሰ ተስፋዬ – ሙጂብ ቃሲም

ተጠባባቂዎች

ጃፋር ደሊል ፣ እሸቱ መና ፣ ኄኖክ ካሳሁን ፣ ዳዋ ሁቴሳ ፣ ሱራፌል ዳኛቸው ፣ ቡልቻ ሹራ ፣ ጥላሁን  ወልዴ
የወልድያ አሰላለፍ
ኤሚክሪል ቤሊንጌ

ዮሀሃንስ ኃየይሉ – አዳሙ መሀመድ – ያሬድ ዘውድነህ – ቢንያም ዳርሰማ

ታዬ አስማረ – ምንያህል ይመር – ያሬድ ሀሰን – ሀብታሙ ሸዋለም

አንዱአለም ንጉሴ – ጫላ ድሪባ

ተጠባባቂዎች

ዳዊት አሰፋ ፣ ሙሉጌታ ወ/ጊዮርጊስ ፣ በድሩ ኑርሁሴን ፣ አለማየሁ ግርማ ፣ ሙሉጌታ ረጋሳ ፣ ሙሉነህ ጌታሁን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *