ቻምፒየንስ ሊግ፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሜዳው ውጪ በጠባብ ውጤት ተሸነፈ

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሜዳው ውጪ በኤምሲ ኤል ኡልማ 1ለ0 በሆነ ጠባብ ውጤት ተሸንፏል፡፡

በጨዋታው ኤል ኡልማዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ፍጱም የሆነ የበላይነት ነበራቸው፡፡ የፈረሰኞቹ አምበል ደጉ ደበበ የመጀመሪያው ግማሽ ሊጠናቀቅ ጥቂት ደቂቃዎች ሲቀሩት ቼኒኒ ላይ በሰራው ጥፋት በተሰጠው ፍጵም ቅጣት ምት ፋሬስ ሃሚቲ በማስቆጠር 1ለ0 በሆነ ውጤት እረፍት ወጥተዋል፡፡

በሁለተኛው አጋማሽ ጊዮርጊሶች ምንም መሻሻል ሳያሳዩ ጨዋታው አጠናቅቀዋል፡፡ ዮጋንዳዊው ግብ ጠባቂ ሮበርት ኦዶንካራ ግብ ሊሆኑ የሚችሉ በርካታ ኳሶችን በማምከን የተሻለ ነበር፡፡ የመልሱ ጨዋታ በባህር ዳር ስታዲየም የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሁለቱ ክለቦች አሸናፊ የጋናው አሻንቲኮቶኮን የሚገጥም ይሆናል፡፡

ያጋሩ