ወልዲያ ሲሳይ ባንጫ እና ለሚ ኢታናን አስፈረመ

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ግርጌ ላይ የሚገኘው ወልዲያ የቀድሞ የሲዳማ ቡና እና ደደቢት ግብ ጠባቂ ሲሳይ ባንጫን እንዲሁም የመብራት ሃይል የመሃል ሜዳ ተጫዋች የነበረው ለሚ ኢታናን ማስፈረሙን ተነግሯል፡፡

ወልዲያ ከፕሪምየር ሊግ ላለመውረድ በሚያደርገው ትግል ላይ ይጠቅሙኛል ያላቸውን ተጨዋቾች መመልመል ከጀመረ ቆየት ብሏል፡፡ ከደደቢት ጋር በውድድር ዘመኑ መጀመሪያ ባለመስማማት የተለያየው ሲሳይ ለወልዲ ለመጫወት መስማማቱ ታውቋል፡፡ ምንም እንኳን ደደቢት እና ወልዲያ በሲሳይ ባንጫ ቀሪ የ6 ወር ውል ዙሪያ ድርድሮች ቀጥሏል፡፡ ወልዲያ በመብራት ሃይል እና የመን በተጫዋችነት ያሳለፈው ለሚ ኢታናም ለወልዲያ መፈረሙ መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡

ወልዲያ ከዳሽን ቢራ አሸናፊ አደምን ለማስፈረም ጥረት ጀምሯል፡፡ የተሻለ ገንዘብ ማቅረብ ከቻሉ ከኢትዮጵያ ቡና ቶክ ጀምስን ማስፈረም እንደሚችሉ ተነግሯል፡፡ ቶክ ጀምስን በውሰት ለመውሰድ ከውልዲያ ሌላ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፈላጊው መሆኑ ይታወሳል፡፡ በተያያዘ ዜና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ቡናውን ኤፍሬም ዘካሪስን በውሰት ለማስፈረም ጥረት ጀምሯል፡፡
ምንጭ ፕላኔት ስፓርት

ያጋሩ