በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 11ኛው ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታዎች ሀሙስ ቀጥለው ሲካሄዱ ወላይታ ድቻ በገዛ ሜዳው ያደረገውን ጨዋታ በአሸናፊነት ተወጥቷል፡፡
ባለፈው እሁድ በኤኤፍሲ ሊዮፓርድስ ተሸንፎ ከኮንፌድሬሽን ዋንጫ የተሰናበተው የገብረመድን ኃይሌ መከላከያ ወደ ቦዲቲ ባደረገው ጉዞ ሽንፈትን አስተናግዶ ተመልሷል፡፡ አዲስ አበባ እና ሶዶ የሚገኙ ደጋፊዎችን ጨምሮ መላው የወላይታ ድቻ ደጋፊ በጉጉገት የጠበቀው ጨዋታ በርካታ ህዝብ ታድሞበት በጣፋጭ የ1-0 ድል ተጠናቋል፡፡ ለድቻ ብቸኛዋን ግብ ከመረብ ያሳረፈው አሸናፊ ሽብሩ በመጀመርያው አጋማሽ ነው፡፡
ከ7 ተከታታይ የአቻ ውጤቶች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ድቻ ነጥቡን ወደ 13 አሳድጎ 6ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡
በ11 አሰት አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ የተጫወቱት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ደደቢት ጨዋታ እንደተጠበቀው ሳይሆን በደካማ እንቅስቃሴ ታጅቦ ያለ ግብ ተጠናቋል፡፡
በጨዋታው ከቻምፒዮንስ ሊግ የሜዳ ውጪ ጨዋታ ማክሰኞ የተመለሰው ደደቢት ተዳክሞ ሆኖ ሲቀርብ እና ለረጅም ጊዜያት ከውድድር የራቁት ንግድ ባንኮች ደግሞ ወደ ጨዋታ ሪትም መግባትና ውህደት ማሳየት ተስኗቸው ታይቷል፡፡
{jcomments on}