ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ወላይታ ድቻ – ቀጥታ የጽሁፍ ስርጭት

ቅዱስ ጊዮርጊስ2-0ወላይታ ድቻ

6′ አቡበከር ሳኒ፣ 79′ አዳነ ግርማ


ጨዋታው በቅዱስ ጊዮርጊስ 2-0 አሸናፊነት ተጠናቋል። ውጤቱም ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ3 ተከታታይ ጨዋታ በኃላ ወደ ድል የተመለሰበት ሆኗል።


90′ ተጨማሪ ሰዓት – 4 ደቂቃ


88′ ራምኬል ከግራ መስመር ያሻማውን ኳስ አዳነ ግርማ በግንባሩ ሞክሮ ግብ ጠባቂው መልሶበታል።


88′ አቡበከር ሳኒ ቺፕ አድርጎ የሞከረውን ኳስ ዳግም ንጉሴ ከመስመር ላይ በመቀስ ምት አውጥቶታል።


86′  የተጫዋች ለውጥ – ወላይታ ድቻ

ፀጋዬ ብርሃኑ ወጥቶ ዮርዳኖስ ዮሐንስ ገብቷል።


84′  የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ

ሳላህዲን ሰዒድ ወጥቶ ተስፋዬ አለባቸው ገብቷል።


79′ ጎል!!!!

አዳነ ግርማ ከራምኬል የተሻማለትን ኳስ አየር ላይ እንዳለ በቮሊ በመምታት ግብ አስቆጥሮ ልዩነቱን አስፍቷል።


77′  የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ

በሃይሉ አሰፋ ወጥቶ ራምኬል ሎክ ገብቷል።


74′ ሳላህዲን ሰዒድ ያገኘውን ነፃ ኳስ ይዞ ከመግባት ይልቅ ከርቀት ለመምታት ቢመርጥም ኳሱን ወንድወሰን መልሶታል።


67′ የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ

አብዱልከሪም ንኪማ ወጥቶ አዳነ ግርማ ገብቷል።


62′ ሳላህዲን ሰዒድ ያገኘውን ግልፅ የግብ ዕድል እንዳይጠቀም ቶማስ ስምረቱ ተንሸራቶ አስጥሎታል።


61′ አቡበከር ሳኒ ከርቀት የመታውን ኳስ ወንድወሰን ይዞበታል።


56′ ዳግም ንጉሴ አብዱልከሪም ንኪማ ላይ አደገኛ ጥፋት ሰርቶ ቢጫ ካርድ አይቷል።


53′ የተጫዋች ለውጥ – ወላይታ ድቻ

ዮሴፍ ድንገቱ ወጥቶ አማኑኤል ተሾመ ገብቷል።


51′ የወላይታ ድቻ ተጫዋቾች ከማዕዘን ምት የተሻማን ኳስ ለማውጣት ሲሞክሩ ባለመግባባታቸው ኳሱ የራሳቸውን ግብ አግዳሚ ታኮ ወጥቷል።


46′ ሁለተኛው የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጀምሯል።


የመጀመሪያው አጋማሽ በቅዱስ ጊዮርጊስ 1-0 መሪነት ተጠናቋል።


45+2′ ሳላዲን ሰዒድ ኳስ ይዞ ወደ ሳጥኑ በመግባት የመታውን ኳስ ወንድወሰን አውጥቶታል።


45′ ተጨማሪ ሰዓት – 2 ደቂቃ


43′ ቶማስ ስምረቱ በሃይሉ ቱሳ ላይ በሰራው ጥፋት ምክኒያት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተሰጥቶታል።


37′ ያስር ሙገሬዋ ፍፁም ቅጣት ምት ለማግኘት አስመስለህ ወድቀሀል በሚል ቢጫ ካርድ ተመልክቷል።


35′ ወላይታ ድቻዎች በተጫዋች መጎዳት ምክኒያት የወጣን ኳስ በስፖርታዊ ጨዋነት ባለመመለሳቸው ደጋፊዎች ተቃውሞ አሰምተዋል።


28′ ሳላህዲን ባርጌቾ ከሳጥኑ ውጪ የሞከረውን ኳስ ወንድወሰን በቀላሉ ይዞታል።


24′ አበባው ቡጣቆ በግምት ከግቡ 35 ሜትር ርቀት አክርሮ የመታው ኳስ ለጥቂት ከግቡ አናት በላይ ወጥቷል።


21′ መሳይ አጪሶ ያሻማው ቅጣት ምት ሳይነካ ወደውጪ ወጥቷል።


19′ ፀጋዬ ብርሃኑ ወደግብ ያሻማውን አደገኛ ኳስ ሮበርት ተቆጣጥሮታል።


16′ አበባው ቡጣቆ የመታው ቅጣት ምት በወንድወሰን ገረመው ተመልሷል።


9′ ያስር ሙገሬዋ ከሳጥኑ ውጪ የመታው ኳስ ከግብ አናት በላይ ወጥቷል።


6′ ጎል!!!!

በሃይሉ አሰፋ ያሻማውን የማዕዘን ምት ናትናኤል ዘለቀ ሲገጨው አቡበከር ሳኒ አግኝቶ በቀላሉ ወደግብ በመቀየር ቅዱስ ጊዮርጊስን መሪ አድርጓል።


1′ ጨዋታው በወላይታ ዲቻ አማካኝነት ተጀምሯል።


ትናንትና ጠዋት ከዚህ ዓለም በሞት ለተለየው ጀግናው አትሌት ምሩፅ ይፍጠር የ1 ደቂቃ የህሊና ፀሎት ተደርጓል።


የመጀመሪያ አሠላለፍ – ቅዱስ ጊዮርጊስ 

30 ሮበርት ኦዶንካራ

15 አስቻለው ታመነ -23 ምንተስኖት አዳነ-13 ሳልሀዲን በርጌቾ-4 አበባው ቡጣቆ

17 ያስር ሙጌርዋ-26 ናትናኤል ዘለቀ-27 አብዱልከሪም ኒኪማ

16 በሀይሉ አሰፋ-7 ሰልሀዲን ሰኢድ -18 አቡበከር ሳኒ


ተጠባባቂዎች

1 ፍሬው ጌታሁን

2 ፍሬዘር ካሣ

19 አዳነ ግርማ

21 ተስፋዬ አለባቸው

10 ራምኬል ሎክ

25 አንዳርጋቸው ይላቅ

12 ደጉ ደበበ


የመጀመሪያ አሠላለፍ – ወላይታ ድቻ

1 ወንድወሰን ገረመው

6 ተክሉ ታፈሰ – 27 ሙባረክ ሽኩር – 3 ቶማስ ስምረቱ

5 ዳግም ንጉሴ – 4 ዮሴፍ ድንገቱ– 17 በዛብህ መለዮ – 21 መሳድ አጪሶ – 9 ያሬድ ዳዊት

19 አላዘር ፋሲካ – 23 ጸጋዬ ብርሃኑ


ተጠባባቂዎች

12 ወንድወሰን አሸናፊ

20 አብዱልሰመድ አሊ

26 ጥላሁን በቶ

13 ዳግም በቀለ

14 ሲሳይ ማሞ

8 አማኑኤል ተሾመ

15 ዮርዳኖስ ዮሐንስ

2 Comments

Leave a Reply