ኢትዮጵያ ቡና ያዘጋጀው የስፖርታዊ ጨዋነት ስትራቴጂክ እቅድ ላይ ውይይት ተካሄደ

የእግር ኳስ ነውጠኝነት እና ረብሻ ማስወገጃ ስትራቴጂ አቀራረብ ሂደት በሚል መሪቃል  የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት የቦርድ ሰብሳቢ መ/አለቃ ፈቃደ ማሞ ፣ የቦርዱ አባላት ፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደት አቶ ጅነይዲ ባሻ ፣ የፌዴሬሽኑ  የስራ አስፈፃሚ አባለት ፣ የፀጥታ ክፍል ሀላፊዎች ፣ የክለቡ ደጋፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ዛሬ በዋቢ ሸበሌ ሆቴል በስፖርታዊ ጨዋነት ስትራቴጂ ፕላን ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተከሄዷል፡፡

የእንኳን ደናህ መጣቹሁ መልዕክት እና የስትራቴጂ እቅዱ በተዘጋጀበትን አላማ ዙርያ ንግግር ያደረጉት መቶ አለቃ ፈቃደ ክለቡ በስፖርታዊ ጨዋነት የማያዳግም እርምት ለመውሰድ ቆርጦ መነሳቱን በመግለፅ የስፖርት ሜዳዎች ሰላማዊና ከረብሻ የፀዱ እንዲሆኑ መልክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በመቀጠል ንግግራቸውን ያቀረቡት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደት አቶ ጁነይዲ ባሻ ኢትዮዽያ ቡና ይህን የስትራቴጂ ዕቅድ አዘጋጅቶ ወደ ትግበራ ለመግባት በዚህ መልኩ መነሳቱ ሊያስመሰግነው ይገባል ብለዋለው ፡፡ አቶ ጁነይዲ አክለውም ይህን እቅድ ሁሉም ክለቦች ሊተገብሩት እንደሚገባና ፌዴሬሽኑም በዘድሮው አመት የእግር ኳስ ሜዳዎቻችን ሰላማዊ እንዲሆኑ በርካታ ስራዎችን መስራቱን ገልፀው ከዚህ በኋላም ከኢትዮዽያ ቡና ጋር ተቀራርበው እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡

አስር ምዕራፍ ፣ ሠላሳ ስድስት ንዑስ ርዕስ ፣ ሠላሳ አምስት የትግበራ መርሀ ግብር ያለውን ስትራቴጂ እቅዱን ያዘጋጁት የቀድሞ የኢትዮዽያ ግር ኳስ ፕሬዝደት የነበሩት አቶ አህመድ ያሲን እቅዱን ለማዘጋጀት ያነሳሳቸውን ምክንያት ሲገልፁ ” እግር ኳሳችን ከቅር አመታት ወዲህ ክፉኛ ታሟል በቶሎ ህክምና ካላኘ ሊሞት ስለሚችል መድሀኒቱ ይሆናል ብዬ ያሰብኩትን ይህን ስትራቴጂ እቅድ ለማዘጋጀት ችያለው፡፡ ” ብለዋል፡፡

አቶ አህመድ ከተሳሳተ አስተሳሰብ ወጥተን እግር ኳስን በእውቀት መደገፍ እንደሚገባ አፅኖት ሰጥተው ይህ ቅድ ለኢትዮዽያ ቡና ክለብ  ብቻ ሳይሆን ሁሉም ክለቦች ቢጠቀሙበት መልካም መሆኑንም ገልዋል፡፡

በመቀጠል በሦስት የተከፈለ የስትራቴጂ እቅዱ ፍሬ ሀሳቦች በተለያዩ ግለሰቦች አማካኝነት  ጥልቅ የሆነ ዳሰሳ ከቀረበ በኋላ ከተሳታፊዎች ጥያቄዎችና አስተያየቶች የተሰጠበት ሲሆን በመጨረሻም ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽ ተሰቶበት የዕለቱ መርሀግብር ፍፃሜውን አግኝቷል፡፡

Leave a Reply