ጅማ አባ ቡና ከ ፋሲል ከተማ | ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

ጅማ አባ ቡና 1-3ፋሲል ከተማ

89′ ሱራፌል አወል | 30′ ኤፍሬም አለሙ 62′ ሰለሞን ገብረመድህን 75′ ኤዶም ሆሮሶውቪ


ተጠናቀቀ !!!
ጨዋታው በእንግዳው ፋሲል ከተማ አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

ጎልልል!!! ጅማ አባ ቡና
89′ ተቀይሮ የገባው ሱራፌል አወል ለጅማ አባ ቡና ግብ አስቆጥሯል፡፡

87′ ፋሲል በሜዳው የሚጫወት በሚመስል ሁኔታ ተመልካቹ በጠቅላላ ድጋፉን እየሰጠው ይገኛል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ፋሲል
ኤዶም ሆሮሶውቪ ወጥቶ ሙሉቀን ታሪኩ ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ፋሲል ከተማ
ያሬድ ዝናቡ ገብቶ ሄኖክ ገምቴሳ ወጥቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ጅማ አባ ቡና
ሀይደር ሸረፋ ወጥቶ ኪዳኔ አሰፋ ገብቷል፡፡

ጎልልል!!! ፋሲል
75′ ኤዶም የጅማ አባቡና ተከላካዮችን አልፎ የፋሲልን 3ኛ ጎል አስቆጠረ፡፡

71′ ፋሲል ከተማዎች ተረጋግተው በሚገባ ብልጫ ወስደውና ኳሱን ተቆጣጥረው እየተጫወቱ ይገኛሉ፡፡

ቢጫ ካርድ
68′ ሀይደር ሸረፋ ሀይል የተቀላቀለበት አጨዋወት በመጫወቱ ቢጫ ካርድ ተመልክቷል፡፡

የተጨዋች ለውጥ – ጅማ አባ ቡና
ቴዎድሮስ ገ/ፃዲቅ ወጥቶ ቢኒያም ሀይሌ ገብቷል፡፡

ደጋፊው በውጤቱ ተከፍቶ ስቴዲዮሙን ለቆ እየወጣ ነው፡፡

ጎልልል!!!! ፋሲል ከተማ
62′ ሰለሞን ገ/መድህን ተቀይሮ ገብቶ በተመሳሳይ ሁኔታ ከ17 ሜትር ርቀት አክሮ መቶ ግሩም ጎል አስቆጠረ፡፡

60′ ቢያድግልኝ ኤልያስ ከ25 ሜትር ርቀት ላይ የተገኘውን ቅጣት ምት መትቶ በአግዳሚው አናት ላይ ወጥቷል፡፡

የተጨዋች ለውጥ – ጅማ አባቡና
ሱራፌል አወል ገብቶ በድሉ መርድ ወጥቷል

55′ ፋሲሎች ጨዋታውን እያቀዘቀዙ በመልሶ ማጥቃት ሲጫወቱ በአንፃሩ ጅማ አባቡናዎች ጎል ለማስቆጠር ተጭነው እየተጫወቱ ይገኛሉ፡፡

የተጨዋች ለውጥ – ፋሲል ከተማ
ግብ አስቆጣሪው ኤፍሬም ወጥቶ ሰለሞን ገብረመድህን ገብቷል፡፡

ተጀመረ!!
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡
– – –
እረፍት!!
የመጀመርያው አጋማሽ በፋሲል ከተማ መሪነት ተጠናቋል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ – 2

ዮሃንስ ሽኩር!!!!!
መሀመድ ናስር የመታውን የፍፁም ቅጣት ምት ዮሃንስ ሽኩር አድኖበታል፡፡

45′ ለጅማ አባ ቡና የፍጹም ቅጣት ምት ተሰጥቷል፡፡

42′ ተመስገን ከአሜ የተሻገረለትን ኳስ በግንባሩ መቶት ዮሐንስ ሽኩር አወጣበት፡፡

39″ አሜ መሀመድ ያለቀለት ኳስ በማይታመን ሁኔታ አመከነ፡፡ የሚገርም የጎል አጋጣሚ ነበር፡፡

ጎልልል!!! ፋሲል ከተማ
30′ ኤፍሬም አለሙ በግምት 17 ሜትር ርቀት የመታው ኳስ በግሩም ሆኔታ ጎል ሆኗል፡፡ ኤፍሬም ባልተገባ ሁኔታ ደስታውን በመግለፁ ቢጫ ካርድ ተመልክቷል፡፡


ቢጫ ካርድ
24′ ቢያድግልኝ ኤሊያስ ኤዶምን በእጁ ጎትቶ በማስቀረቱ የዕለቱ ዳኛ ቢጫ ሰጥተውታል፡፡

ቢጫ ካርድ
18′ ኤርሚያስ ሀይሉ በሰራው ጥፋት የጨዋታውን የመጀመርያውን ቢጫ ተመልክቷል፡፡

13′ ናትናኤል ጋንጂላ በግራ እግሩ አክሮ የመታውን ኳስ ጀማል ጣሳው እንደምንም ይዞበታል፡፡

8′ በአንድ ሁለት ቅብብል አሜ መሀመድ ያገኘውን ኳስ በጥሩ ሁኔታ ቢመታውም በጎሉ አናት ወጣበት፡፡

3′ ኤዶም ከቀኝ መስመር የተጣለለትን ኳስ አግኝቶ መሬት ለመሬት የመታው ኳስ ለጥቂት ወጣበት፡፡ የጨዋታው የመጀመርያ ጥሩ ሙከራ!

ተጀመረ!!!
ጨዋታው በፋሲል ከተማ አማካኝነት ተጀምሯል፡፡

በታይላንድ ባንኮክ ህክምናውን ሲከታተል ቆይቶ ከቀናት በፊት የተመለሰው አሰልጣኝ ዘማሪያም ወልደጊዮርጊስ ዛሬ ከጅማ አባቡና ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ ላይ ክለቡን በአሰልጣኝነት ለመምራት ተገኝቷል፡፡


የጅማ አባ ቡና አሰላለፍ

22 ጀማል ጣሰው

5 ጀሚል ያዕቆብ – 12 ቢያድግልኝ ኤልያስ – 21 በኃይሉ በለጠ – 3 ተመስገን ደረሰ

4 ሀይደር ሸረፋ – 27 ክርቶፈር ንታንቢ – 15 ቴዎድሮስ ገብረጻዲቅ – 7 በድሉ መርዕድ

9 አሜ መሀመድ – 25 መሀመድ ናስር (አምበል)

ተጠባባቂዎች

1 ሙላቱ አለማየሁ

18 ኃይለየሱስ ብርሃኑ

8 ሱራፌል አወል

10 ቴዎድሮስ ታደሰ

14 ሂድር ሙስጠፋ

17 ቢንያም ኃይሌ

– – – –

የፋሲል ከተማ አሰላለፍ
93 ዮሃንስ ሽኩር

13 ሰኢድ ሁሴን – 16 ያሬድ ባዬ- 14 ከድር ኸይረዲን – 21 አምሳሉ ጥላሁን

17 ይስሃቅ መኩሪያ – 26 ሄኖክ ገምተሳ – 6 ኤፍሬም አለሙ

99 ኤርምያስ ሃይሉ – 9 ኤዶም ሆሮሶውቪ – 20 ናትናኤል ጋንጂላ

ተጠባባቂዎች

1.ምንተስኖት አሉ
4.ፍቅረሚካኤል አለሙ
10.ሙሉቀን ታሪኩ
24 ያሬድ ዝናቡ
3.ሱሌይማን አህመድ
7.ፍፁም ከበደ

56 ገዛኸኝ እንዳለ

1 Comment

Leave a Reply