አዲስ አበባ ከተማ ከ ደደቢት | ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

አዲስ አበባ ከተማ0-1ደደቢት

85′ ኤፍሬም አሻሞደደቢት በ85ተኛው ደቂቃ ኤፍሬም አሻሞ ባስቆጠረው ግብ ታግዞ ጨዋታውን ማሸነፍ ችሏል።


90′ ተጨማሪ ሰዐት – 4 ደቂቃ


89′ ዳዊት ማሞ ከማዕዘን ምት የተሻማውን ኳስ በግንባሩ ቢሞክርም ኳሱ በራሱ ቡድን ተጫዋቾች ተመልሷል።


88′ አዲስ አበባ ከተማዎች ግብ ካስተናገዱ በኃላ አቻ ለመሆን ከርቀት በአማረ እና ዘሪሁን አማካኝነት ሙከራዎችን አድርገዋል።


85′ ጎል!!!!

ኤፍሬም አሻሞ ከጌታነህ የተቀበለውን ኳስ ይዞ ከገባ በኃላ ወደግብ በመቀየር ደደቢትን መሪ አድርጓል።

83′ አማረ በቀለ የዳኛን ውሳኔ በፀጋ ባለመቀበሉ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል።
80′ ዳዊት ፍቃዱ ያሻማውን የማዕዘን ምት ስዩም ተስፋዬ በግንባሩ ሞክሮ ወደውጪ ወጥቶበታል።


78′ የተጫዋች ለውጥ – አዲስ አበባ ከተማ

ፍቃዱ አለሙ ወጥቶ ኤፍሬም ቀሬ ገብቷል።


77′ አስራት መገርሳ አደገኛ አጨዋወት በመጫወቱ ቢጫ ካርድ ተሰጥቶታል።


76′ የተጫዋች ለውጥ – ደደቢት

ሺመክት ጉግሳ ወጥቶ አቤል ያለው ገብቷል።


75′ ዳዊት ማሞ ያቀበለውን ኳስ ፍቃዱ አለሙ ከጠባብ አንግል ሞክሮ ወደውጪ ወጥቶበታል።


73′ የአዲስ አበባ ከተማ ተጫዋቾች በተደጋጋሚ ከጨዋታ ውጪ አቋቋም ላይ እየተያዙ ይገኛሉ።


63′ ዳዊት ፍቃዱ በሳጥኑ ውስጥ ጥፋት ተሰራብኝ ብሎ ቢወድቅም ዳኛው በዝምታ አልፈዋል።


61′ የተጫዋች ለውጥ – አዲስ አበባ ከተማ

ዮናታን ብርሃነ ወጥቶ እንየው ካሳሁን ገብቷል።


58′ ደደቢቶች በጥሩ ቅብብል ይዘው የገቡትን ኳስ ሺመክት ጉግሳ ሞክሮ ለትንሽ ወደውጪ ወጥቷል።


54′ ጌታነህ ከበደ ከ25 ሜትር ርቀት የመታው ቅጣት ምት የግቡን አግዳሚ መትቶ ወጥቷል።


50′ የተጫዋች ለውጥ – ደደቢት

ሳምሶን ጥላሁን ወጥቶ ኤፍሬም አሻሞ ገብቷል።


48′ አስራት መገርሳ በጥሩ ሁኔታ አልፎ ያሻማውን ኳስ ጌታነህ አግኝቶ ቢመታውም ግብ ጠባቂው አውጥቶታል።


46′ ሁለተኛው የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጀምሯል።


የመጀመሪያው አጋማሽ ግብ ሳይቆጠርበት በአቻ ውጤት ተጠናቋል።


45′ ተጨማሪ ሰዐት – 3 ደቂቃ


40′ ዳዊት ፍቃዱ ከሳምሶን ጥላሁን በረጅሙ የተጣለለትን ኳስ ሞክሮ ወደውጪ ወጥቶበታል።


35′ የተጫዋች ለውጥ – አዲስ አበባ ከተማ

አዳነ በላይነህ (በጉዳት) ወጥቶ አለማየሁ ሙለታ ገብቷል።


29′ አዲስ አበባ ከተማ ከመስመር በሚሻሙ ኳሶች ተጠቅሞ ግብ ለማስቆጠር እየሞከሩ ይገኛሉ።


21′ አማረ በቀለ የበረኛውን መውጣት አይቶ ከርቀት የመታው ኳስ ወደውጭ ወጥቷል።


20′ ዳዊት ማሞ ከዮናታን የተላከለትን ኳስ ቢሞክርም ግብ ማስቆጠር አልቻለም።


19′ ሺመክት ጉግሳ ሁለት ተጫዋቾችን አልፎ የመታውን ኳስ ግብ ጠባቂው በቀላሉ ይዞታል።


15′ አማረ በቀለ ጉዳት ቢያስተናግድም የህክምና ዕርዳታ ተደርጎለት ጨዋታውን ቀጥሏል።


10′ ሁለቱም ቡድኖች ለአጥቂዎቻቸው የተመጠነ ኳስ ማድረስ ተስኗቸዋል።


3′ ዳዊት ፍቃዱ በግንባር የሞከረው ኳስ ከግቡ አግዳሚ በላይ ወጥቷል።


1′ ጨዋታው በደደቢት አማካኝነት ተጀምሯል።


ታህሳስ 14 ቀን  2009 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት ለተለየው ጀግናው አትሌት ሻምበል ምሩፅ ይፍጠር የ1 ደቂቃ የህሊና ፀሎት ተደርጓል።


የመጀመሪያ  አሰላለፍ – ደደቢት

33 ክሌመንት አሺቴይ

7 ስዩም ተስፋዬ — 15 ደስታ ደሙ –14 አክሊሉ አየነው — 10 ብርሃኑ ቦጋለ

24 ከድር ኩሊባሊ — 4 አስራት መገርሳ — 8 ሳምሶን ጥላሁን — 19 ሽመክት ጉግሳ 

 9 ጌታነህ ከበደ — 17 ዳዊት ፍቃዱ


ተጠባባቂዎች

22 ታሪክ ጌትነት

11 አቤል ያለው

21 ኤፍሬም አሻሞ

18 አቤል እንዳለ

27 እያሱ ተስፋዬ

20 የአብስራ ተስፋዬ

16 ሰለሞን ሐብቴ


የመጀመሪያ አሰላለፍ – አዲስ አበባ ከተማ

98 ደረጀ ዓለሙ

80 አዳነ በላይነህ – 20 ሰይፈ መገርሳ – 70 ዲሚጥሮስ ወልደስላሴ – 77 አማረ በቀለ

40 ዳዊት ማሞ – 13 ዘሪሁን ብርሃኑ – 83 ፀጋ አለማየሁ – 90 አቤል ዘውዱ – 10 ዮናታን ብርሃነ

24 ፍቃዱ አለሙ


ተጠባባቂዎች 

1 ተክለማርያም ሻንቆ

30 መሀጅር መኪ

81 አለማየሁ ሙለታ

6 ጊት ጋትኮች

7 ኤፍሬም ቀሬ

8 ኃይሌ እሸቱ

2 እንየዉ ካሳሁን


Leave a Reply