ከ23 አመት በታች ቡድኑ በሜዳው ተሸነፈ

የኢትዮጵያ ከ23 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን ከሱዳን አቻው ጋር ባደረገው የ2015 የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ማጣርያ 2-1 ተሸንፏል፡፡

ድሬዳዋ ላይ በተደረገው ጨዋታ ሱዳኖች ኦስማን በ27ኛው ደቂቃ እንዲሁም ጣሒር በ40ኘው ደቂቃ ባስቆጠሯቸው ግቦች የመጀመርያውን አጋማሽ በ2-0 መሪነት አጠናቀዋል፡፡

ሱዳኖች የመጨረሻዎቹን 10 ደቂቃዎች በጎዶሎ ልጆች የተጫወቱ ቢሆንም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ግብ ማስቆጠር የቻለው ግን ጨዋው ሊጠናቀቅ የ2 ደቂቃዎች እድሜ ሲቀረው ነው፡፡ በ91ኛው ደቂቃ በሱዳን የግብ ክልል በእጅ የተነካችውን ኳስ ተከትሎ የተሰጠውን የፍፁም ቅጣት ምት ዳዋ ሁጤሳ ከመረብ አሳርፎ ጨዋታው በእንግዳው ሱዳን 2-1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

የመልሱ ጨዋታ ከ2 ሳምንታት በኋላ በኦባዬድ ከተማ ይካሄዳል፡፡ ኢትዮጵያ የሜዳዋን ሽንፈት ቅልብሳ ወደተከታዩ ዙር ካለፈችም ደቡብ አፍሪካን ትገጥማለች፡፡

ያጋሩ