የጨዋታ ሪፖርት | ወልድያ 0-0 ሲዳማ ቡና

በ7ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መልካ ቆሌ ላይ ሲዳማ ቡናን ያስተናገደው ወልድያ ያለ ግብ ጨዋታውን አጠናቋል፡፡
ጨዋታው የተጀመረው እንደሌሎቹ ጨዋታዎች ሁሉ ከትላንት በስቲያ ከዚህ አለም በሞት ለተለየው ጀግናው አትሌት ምሩፅ ይፍጠር የህሊና ጸሎት በማድረግ ነበር፡፡

በጨዋታው ወልድያ የእንቅስቃሴ የበላይነት ማሳየት እና ያለቀላቸው የግብ ሙከራዎችን ማድረግ ቢችሉም 3 ነጥብ የሚያስገኝላቸውን ግብ ማግኘት አልቻሉም፡፡ ታይተዋል።

ወልድያዎች የግብ ሙከራ ማድረግ የጀመሩት ገና በመጀመሪያው ደቂቃ ነበር፡፡ አንዱአለም ንጉሴ ከቦክሱ ግራ ጠርዝ ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ አድርጓል። በ4ኛው ደቂቃ ደግሞ ለጫላ የተሻገረለትን ኳስ የሲዳማው ግብ ጠባቂ ከግብ ክልሉ ወጥቶ ያዳነው ሲሆን የተገኘውን የማእዘን ምት አምበሉ ዮሃንስ ኃይሉ በግምባሩ በመግጨት ሞክሮ የሲዳማ ተጫዋቾች እንደምንም አድነውታል። በ26 ደቂቃ ከቅጣት ምት የተሻገረውን ኳስ አንዱአለም በመዘግየቱ ሳይጠቀምበት የቀረውም በመጀመርያው አጋማሽ ከተፈጠሩ የግብ እድሎች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

ሲዳማ ቡናዎች በመጀመርያው አጋማሽ የግብ ሙከራ ለማድረግ ረጅም ደቂቃዎች ለመጠበቅ ተገደዋል፡፡ በ45 ደቂቃ አንተነህ ተስፋዬ ከርቀት የሞከረው ኳስ በግቡ አግዳሚ በላይ ወደ ውጭ የወጣበት በሲዳማ በኩል የሚጠቀስ ሙከራ ነበር፡፡

 

ከእረፍት መልስ ልክ እንደመጀመሪያው አጋማሽ አደጋ መፍጠራቸውን

የቀጠሉት ወልዲያዎች በ46ኛው ደቂቃ ሙሉጌታ ረጋሳ ከመሀል ሜዳ ፍጥነቱን

ተጠቅሞ የሲዳማ ተጫዋቾችን ካለፈ በኋላ ከሳጥኑ የግራ ጠርዝ መሬት ለመሬት የመታው ኳስ ለጥቂት ወደ ውጭ ወጥታለች። ሲዳማዎችም በ57ኛው ደቂቃ የሲዳማው ግብ ጠባቂ ፈጥሮት የነበረውን ስህተት በቅርብ የነበሩት አጥቂዎች ሳይጠቀሙበት ቀርተዋል።

ሲዳማዎች የመጀመሪያ ኢላማውን የጠበቀ አደገኛ ሙከራቸውን በ80 ደቂቃ ያደረጉ ሲሆን ከግራ መስመር በኩል ያደረጉትን ሙከራ ኤሚክሪል ቢሌንጌ አድኖታል።

በ87 ደቂቃ በጨዋታው ጥሩ የተንቀሳቀሰው ሀብታሙ ሸዋለም ያሻማውን ኳስ በሚገርም ሁኔታ ወልድያዎች ሳይጠቀሙበት የቀረ ሲሆን ከተፈጠሩት የግብ አጋጣሚዎችም ለግብ የቀረበች እና የምታስቆጭ

ነበረች።

ጨዋታው በወልድያ የበላይነት እና ያለቀላቸው የግብ ማግባት አጋጣሚዎች የታጀበ ቢሆንም ያለ ጎል ተጠናቋል።

በጨዋታው ወቅት በቀኝ ጥላ ፎቅ አካባቢ ተገቢ ያልሆኑ እና የጨዋታውን ድባብ ሲያበላሹ የነበሩ መጥፎ ቃላትን መሰንዘር እና አንዳንድ የስፖርታዊ ጨዋነት ችግሮች ተስተውሏል።

Leave a Reply