ኢትዮጵያ ቡና ከዳሸን ቢራ – ዳሰሳ

ቀን ቅዳሜ 08 የካቲት 2006

ቦታ – አበበ ቢቂላ ስታዲየም

የጨዋታ መጀመርያ ሰአት – 10፡00

ይህ ጨዋታ የሳምንቱ ታላቅ ጨዋታ ነው፡፡ የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና ተጫዋች እና አሰልጣኝ ካሊድ መሃመድ ዳሸንን ይዞ የቀድሞ ክለቡን ለመጀመርያ ጊዜ በሚገጥምበት ጨዋታ ባለፈው ሳምንት ያስመዘገበውን የመጀመርያ የሊግ ድል ለመድገም ይፋለማል ፡፡

ኢትዮጵያ የቅርብ ጊዜ አቋሙ መልካም አይደለም፡፡ ተከታታይ ጨዋታዎችን አቻ ሲለያይ ከመሪው ያለው የነጥብ ልዩነት ወደ 14 ሰፍቷል፡፡ አደገኞቹ በፍጥነት ወደ አሸናፊነት ካልተመለሱ የውድድር ዘመኑ ዳገት እንዳይሆንባቸው ያሰጋል፡፡

ዳሸን ባለፈው ሳምንት መብራት ኃይልን 1-0 አሸንፎ በከፍተኛ መነቃቃት ላይ ሲገኝ ኢትዮጵያ ቡና በበኩሉ ወደ አሰላ ተጉዞ በአቻ ውጤት ተመልሷል፡፡

ጠቃሚ ነጥቦች

-ዳሸን በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ 11ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ኢትዮጵያ ከዳሽን በ2 ነጥቦች እና ደረጃዎች ከፍ ብሎ 9ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

-ሁለቱ ቡድኖች በሊጉ ሲገናኙ ይህ ለመጀመርያ ጊዜ ነው፡፡

– ዳሸን ቢራ በቅድመ ውድድር ዝግጅት ኢትዮጵያ ቡናን አበበ ቢቂላ ስታዲየም ላይ በፍፁም ደስይበለው ብቸኛ ግብ 1-0 ማሸነፉ ይታወሳል፡፡

{jcomments on}

ያጋሩ