ያስር ሙገርዋ ከዩጋንዳ የአፍሪካ ዋንጫ ቡድን ውጪ ሆኗል

የቅዱስ ጊዮርጊሱ አማካይ ያስር ሙገርዋ ከዩጋንዳ የአፍሪካ ዋንጫ ብሄራዊ ቡድን ውጪ ሆኗል፡፡

ያስር ከክለብ አጋሩ ሮበርት ኦዶንካራ ጋር ነበር ወደ ግዜያዊው የዩጋንዳ ብሄራዊ ቡድን የተጠራው፡፡ ሆኖም ሰርቢያዊው ሰርዮቪች ሚሉቲን ሚቾ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ለፈረሰኞቹ በቋሚ አሰላለፍ ውስጥ ገብቶ ለመጫወት የቸገረውን ያስርን ቀንሰዋል፡፡

ሚቾ 9 በዩጋንዳ አዛም ፕሪምየር ሊግ የሚጫወቱ ተጫዋቾችን የቀነሱ ሲሆን በአማካይ ስፍራ ላይ ጥራት ያላቸው ተጫዋቾችን መያዛቸው ምንአልባትም የያስርን የአፍሪካ ዋንጫ ተስፋ ያጨለመ ይመስላል፡፡ ያስር ከደቡብ አፍሪካው ኦርላንዶ ፓይሬትስ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ፈረሰኞቹን ከተቀላቀለ በኃላ በፕሪምየር ሊግ በቋሚ አሰላለፍ ውስጥ የገባው ክለቡ ወላይታ ድቻን 2-0 ባሸነፈበት የ7ተኛ ሳምንት ጨዋታ ነው፡፡ ያስር ከግብ ጠባቂው ሮበርት ጋር በግሉ ልምምዶችን ሲሰራ ነበር፡፡

ዩጋንዳ ክሬንሶቹ ለዝግጅት እና ለአቋም መለኪያ ጨዋታ ወደ ቱኒዚያ 22 ተጫዋቾችን ይዘው አቅንተዋል፡፡ 4 ተጫዋቾች (ሮበርት ኦዶንካራን ጨምሮ) በቀጥታ ቡድኑን ቱኒዚያ ላይ የሚቀላቀሉ ሲሆን ኦዶንካራ ከሸገር ደርቢ በኃላ ወደ ቱኒዚያ የሚያቀና ይሆናል፡፡ ከ26ቱ ተጫዋቾች 23ቱ ዩጋንዳን ከ39 ዓመት በኃላ በአፍሪካ ዋንጫው የሚወክሉ ይሆናል፡፡

የተመረጡ ተጫዋቾች ዝርዝር

ሮበርት ኦዶንካራ፣ ቤንጃሚን ኦቻን፣ ጀማል ሳሊም፣ ዴኒስ ኢጉማ፣ ኒኮላስ ዋዳዳ፣ ጆሴፍ ኦቻያ፣ ሻፊቅ ባታምቡዚ፣ ሙሩሺድ ጁኮ፣ አይዛክ ኢዜንዴ፣ ሃሰን ዋሳዋ፣ ቲሞቲ አዋኒ፣ ካሊድ አዎቾ፣ ማይክ አዚራ፣ ቶኒ ማዊጄ፣ ጅኦፍሪ ኪዚቶ፣ ሞሰስ ኦሎያ፣ ሙዛሚል ሙትያባ፣ ጎድፍሬ ዋሉሲምቢ፣ ዊሊያም ኪዚቶ፣ ኢድሪሳ ሉቤጋ፣ መሃመድ ሻባን፣ ጂኦፍሪ ሴሬንኩማ፣ ፋሩክ ሚያ፣ የኑስ ሴንታሙ፣ ጂኦፍሪ ማሳ እና ዴኒስ ኦኒያንጎ

Leave a Reply