ደደቢት ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

FT ደደቢት   2-1  ኢት. ንግድ ባንክ

19′ 45+1′ ጌታነህ ከበደ | 63′ አዲሱ ሰይፉ


ተጠናቀቀ!!
ጨዋታው በደደቢት አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ ሰማያዊዎቹ ለጊዜውም ቢሆን የደረጃ ሰንጠረዡን አናት ተቆናጠዋል፡፡

ቢጫ
90+4′ ዳዊት ፍቃዱ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ – 3 

88′ ጨዋታው የተቀዛቀዘ እንቅስቃሴ እየታየበት ይገኛል፡፡

ቢጫ
79′ ጂብሪል አህመድ በኤፍሬም ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

77′ ጨዋታው በተደጋጋሚ በሚሰሩ ጥፋቶቸች እየተቆራረጠ ይገኛል፡፡

67′ ኤፍሬም አሻሞ በተከላካዮች መሀል አምልጦ የሞከረውን ኳስ ፌቮ አድኖታል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ባንክ
66′ ታድዮስ ወልዴ ወጥቶ ሞላለት ያለው ገብቷል፡፡

ጎልልል!!! ባንክ!!!
63′ አዲሱ ሰይፉ ከግራ መስመር አቅጣጫ ግመማሽ ጨረቃው አቅራብያ የተገኘውን ቅጣት ምት በቀጥታ መትቶ ወደ ግብነት ቀይሮታል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ደደቢት
61′
አቤል እንዳለ ወጥቶ ሰለሞን ሐብቴ ገብቷል፡፡

58′ ጌታነህ ከበደ የግብ ጠባቂው ፌቮን አቋቋም ተመልክቶ ቺፕ ያደረገው ኳስ የላይኛውን መረብ ታኮ ወጥቷል፡፡ ግሩም ሙከራ!

57′ ንግድ ባንክ ወደ ጨዋታው ለመመለስ በመጣር ላይ ይገኛል፡፡ የደደቢትን የተከላካይ መስመር ማስከፈት ባይችሉም በኳስ ቁጥጥር የተሻለ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡

56′ ሳሙኤል ዮሃንስ ከመስመር ያሻገረለትን ግልጽ የጎል ማስቆጠር እድል ዳኛቸው በቀለ ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡

ቢጫ
48′
ካድር ኩሊባሊ የጨዋታውን የመጀመርያ ማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

ተጀመረ!
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡

የእረፍት ሰአት የተጫዋች ለውጥ – ባንክ
ዳንኤል አድሃኖም ወጥቶ ሳሙኤል ዮሃንስ ገብቷል፡፡


እረፍት!!!
የመጀመሪያው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በደደቢት መሪነት ተጠናቋል፡፡

ጎልልል!!! ደደቢት!!!
45+1′ ዳዊት ፍቃዱ ያሻገረለትን ጣጣውን የጨረሰ ኳስ ጌታነህ ወደ ግብ ቀይሮታል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ – 1

37′ ብርሃኑ ቦጋለ ያሻማውን ኳስ ጌታነህ ከበደ በግምባሩ በመግጨት ሞክሮ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡

31′ ከቢንያም በላይ የተሻገረውን ኳስ ታድየዮስ ወልዴ በግምባሩ በመግጨት ሞክሮ በግቡ አግዳሚ ለጥቂት ወጥቷል፡፡ ግሩም ሙከራ !

24′ ከግራ መስመር የፍፁም ቅጣት ምት ጠርዝ ወደ ግብ የሞከረው ኳስ በግቡ አናት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

ጎልልል!!!! ደደቢት !!!
19′ ኤፍሬም ወደ ግብ ያሻገረውን ኳስ ጌታነህ ወደ ግብነት በመቀየር ደደቢትን ቀዳሚ አድርጓል፡፡

12′ ብርሃኑ ቦጋለ ያሻማውን የማዕዘን ምት ሽመክት በጭንቅላቱ በመግጨት ሞክሮ ለጥቂት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

5′ ዳዊት ፍቃዱ ተከላካዮችን አምልጦ የሞከረውን ኳስ ፌቮ መልሶበታል፡፡ የተመለሰውን ኳስ ኤፍሬም መትቶ በግቡ አናት ወደ ውጪ ሰዶታል፡፡

ተጀመረ
ጨዋታው በንግድ ባንክ አማካኝነት ተጀምሯል፡፡


የመጀመሪያ  አሰላለፍ – ደደቢት

33 ክሌመንት አሺቴይ

7 ስዩም ተስፋዬ — 15 ደስታ ደሙ –14 አክሊሉ አየነው — 10 ብርሃኑ ቦጋለ

21 ኤፍሬም አሻሞ – 24 ከድር ኩሊባሊ — 18 አቤል እንዳለ — 19 ሽመክት ጉግሳ

9 ጌታነህ ከበደ — 17 ዳዊት ፍቃዱ

ተጠባባቂዎች

22 ታሪክ ጌትነት

11 አቤል ያለው

27 እያሱ ተስፋዬ

12 ሄኖክ መርሻ

16 ሰለሞን ሐብቴ

25 ብርሀሃኑ አሻሞ


አሰላለፍ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

1 – ኢማኑኤል ፌቮ

 12 አቤል አበበ – 16 ቢኒያም ሲራጅ – 7 ዳንኤል አድሃኖም

15 አዲሱ ሰይፋ – 88 ታዲዮስ ወልዴ – 4 ጅብሪል አህመድ – 21 ዮናስ ገረመው- 80 ቢኒያም በላይ 

10 ዳኛቸው በቀለ

ተጠባባቂዎች

29 ሙሴ ገብረኪዳን

26 ጌቱ ረፌራ

14 ሳየይ ዋጆ

8 ኤፍሬም ካሳ

19 ፍቃዱ ደነቀ

13 ሳሙኤል ዮሀንስ

44 ሞላለት ያለው

Leave a Reply