ቅድመ ዳሰሳ | ሙገር ሲሚንቶ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ

ቀን – የካቲት 6 ቀን 2006

ስታዲየም – ደራርቱ ቱሉ (አሰላ)

የጨዋታ መጀመርያ ሰአት – 09፡00

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ቀትር ላይ በተስተካካይ ጨዋታ ሲቀጥል የሊጉ መሪ ከ ሙገር ሲሚንቶ ጋር ይገናኛል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ እሁድ ወደ አርባምንጭ ተጉዞ በኡመድ ኡኩሪ ብቸኛ ግብ 1-0 ሲያሸንፍ ሙገር ሲሚንቶ በበኩሉ በሜዳው ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ያለግብ መለያየቱ ይታወሳል፡፡

ፕሪሚየር ሊጉን በ21 ነጥቦች ለሚመራው ቅዱስ ጊዮርጊስ የውድድር አመቱ ቀላል ሆኖለታል፡፡ እስካሁን በ7 ተከታታይ የሊግ ግጥሚያዎች በአንድ አጋጣሚ ብቻ መረቡን አስደፍሮ ሁሉንም በድል ተወጥቷል፡፡ ሙገር ዘንድሮም እንደ ቀድሞው ወጥ አቋም ማሳየት ተስኖት በደረጃ ሰንጠረዡ ወገብ እየዋለለ ይገኛል፡፡

ጠቃሚ ነጥቦች

ሁለቱ ቡድኖች እንዲጫወቱ ፕሮግራም የወጣላቸው ጥቅምት 17 ቀን 2006 ፣ 1ኛው ሳምንት ላይ ቢሆንም ቅዱስ ጊዮርጊስ በርካታ ተጫዋቾች ለብሄራዊ ቡድን በማስመረጡ ጨዋታው በተስተካካይ ጨዋታ መልክ ከ4 ወራት በኃላ ይካሄዳል፡፡

-ሁለቱ ቡድኖች ዘንድሮ ሲገናኙ ለ2ኛ ጊዜ ነው፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የምድብ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ 1-0 ሲረታ ፍፁም ገብረማርያም በቀድሞ ክለቡ ላይ ብቸኛዋን ግብ ማስቆጠሩ ይታወሳል፡፡

-ቅዱስ ጊዮርጊስ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ አናት ላይ ሆኖ ወደ አሰላ ሲያቀና ሙገር ሲሚንቶ ከፈረሰኞቹ በ10 ነጥቦች አንሶ 6 ደረጃ ላይ ተቀምጦ ጨዋታውን ያደርጋል፡፡

-ሙገር ካሸነፈ ነጥቡን ወደ 14 አድርሶ 5ኛ ደረጃን ከደደቢት የመረከብ እድል አለው፡፡

-ሙገር በሜዳው 5 ጨዋታዎችን አድርጎ ማሸነፍ የቻለው 1 ብቻ ነው፡፡

-አሰላ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ፈታኝ ከሆኑ ጉዞዎች ዋነኛው ነው፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ1991 ጀምሮ ሙገርን በጎበኘባቸው 13 አጋጣሚዎች ድል አድርጎ የተመለሰው 4 ጊዜ ብቻ ነው፡፡

የእርስ በእርስ ግንኙነቶች

ተጫወቱ – 28

ሙገር አሸነፈ – 6

አቻ – 6

ቅዱስ ጊዮርጊስ አሸነፈ – 16

ሙገር አስቆጠረ – 26

ቅዱስ ጊዮርጊስ አስቆጠረ – 43

{jcomments on}