ዳሸን ቢራ ከ መብራት ኃይል

ቀን ፡ እሁድ የካቲት 2 ቀን 2006 አም.

ስታዲየም ፡ ፋሲለደስ ስታዲየም

የጨዋታ መጀመርያ ሰአት – 9፡00

በክረምቱ የዝውውር ሪኮርድ ጭምር ሰብሮ በርካታ ሚልዮን ብሮች ያፈሰሰው ዳሸን ቢራ እንደተጠበቀው በሊጉ ተፎካካሪ መሆን አልቻለም፡፡ በሊጉ ግብ ማስቆጠር ያለቻለው ዳሸን ቢራ አሰልጣኙን አሰናብቶ ካሊድ መሃመድን የሾመ ሲሆን መብራት ኃይልም በተመሳሳይ በውጤት ማጣት ዮርዳን ስቶይኮቭን አሰናብቶ አጥናፉ አባተን ቀጥሯል፡፡

የሊጉ የመጨረሻ ደረጃን የያዙት ሁለቱ ክለቦች ከአስቸጋሪ የውድድር ዘመን ጉዟቸው ለመውጣት ከእረፍት መልስ የተጀመረውን ፕሪሚየር ሊግ ሊጠቀሙበት ይገባል፡፡

ጠቃሚ ነጥቦች

የመብራት ኃይል ውድ ልጅ የነበረው አስራት መገርሳ ጥርሱን የነቀለበት የቀድሞ ክለቡን በዳሸን መለያ ለመጀመርያ ጊዜ ይገጥማል፡፡ ከአማካዩ በተጨማሪ ዮናታን ከበደ እና መስፍን ወንድሙ በክረምቱ መስኮት መብራት ኃይልን ከለቀቁ ወዲህ ለመጀመርያ ጊዜ የቀድሞ ክለባቸውን ይገጥማሉ፡፡

ሁለቱ ክለቦች በሊጉ ሲገናኙ ይህ ለመጀመርያ ጊዜ ነው፡፡

መብራት ኃይል በደረጃ ሰንጠረዡ መቸረሻ ላይ ሲገኝ ዳሸን ቢራ ከመብራት በአንድ ደረጃ ከፍ ብሎ 13ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

ዳሸን ምንም ግብ ያላስቆጠረ ብቸኛው የፕሪሚየር ሊግ ቡድን ሲሆን መብራት ኃይል ደግሞ 12 ግብ በማስተናገድ ብዙ ግቦች የተቆጠሩበት የፕሪሚየር ሊግ ቡድን ነው፡፡

{jcomments on}

ያጋሩ