ሐዋሳ ከተማ ከ ወላይታ ድቻ | ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

Read Time:2 Minute, 38 Second

FTሐዋሳ ከተማ3-3ወላይታ ድቻ

33′ ጃኮ አራፋት፣ 40′  55′ ፍሬው ሰለሞን  ||  24′ መላኩ ወልዴ (በራሱ ላይ)፣ 28′ ቶማስ ስምረቱ፣ 89′ አላዛር ፋሲካጨዋታው 3-3 በሆነ አቻ ውጤት ፍፃሜውን አግኝቷል።


90′ ተጨማሪ ሰዐት – 4 ደቂቃ


89′ ጎል!!!!

በዛብህ መለዮ ከመስመር ያሻገረውን ኳስ አላዛር ፋሲካ አስቆጥሮ ወላይታ ድቻን አቻ አድርጓል።


87′ የተጫዋች ለውጥ – ሐዋሳ ከተማ

ኤፍሬም ዘካርያስ ወጥቶ ወንድሜነህ አይናለም ገብቷል።


86′ የሐዋሳ ከተማው ኤፍሬም ዘካሪያስ እና የወላይታ ድቻው አላዛር ፋሲካ በፈጠሩት ግጭት ምክንያት ቢጫ ካርድ አይተዋል።


85′ የተጫዋች ለውጥ – ሐዋሳ ከተማ

አረፋት ጃኮ ወጥቶ ፍርዳወቅ ሲሳይ ገብቷል።
81′ የተጫዋች ለውጥ – ወላይታ ድቻ

ሙባረክ ሽኩር ወጥቶ እንዳለ መለዮ ገብቷል።


66′ ሐዋሳ ከተማ ተጨማሪ ግብ ለማስቆጠር ጫና አድርጎ በመጫወት ላይ ይገኛል።


60′ የተጫዋች ለውጥ – ሐዋሳ ከተማ

መድሀኔ ታደሰ ወጥቶ እስራኤል እሸቱ ገብቷል።


55′ ጎል!!!!

ፍሬው ሰለሞን የተሰጠውን ፍፁም ቅጣት ምት በአግባቡ ተጠቅሞ ሐዋሳን መሪ አድርጓል።


54′ ሙባረክ ሽኩር በሳጥኑ ውስጥ ኤፍሬም ላይ በሰራው ጥፋት ምክንያት ፍፁም ቅጣት ምት ለሐዋሳ ከተማ ተሰጥቷል።


52′ የተጫዋች ለውጥ – ወላይታ ድቻ

ዳግም በቀለ ወጥቶ ፈቱዲን ጀማል ገብቷል።


46′ ሁለተኛው የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጀምሯል።


የመጀመሪያው አጋማሽ 2-2 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቀቀ።


45′ ተጨማሪ ሰዐት – 3 ደቂቃ


43′ ሐዋሳ ከተማዎች ተጨማሪ ግብ ለማስቆጠር ጫና ፈጥረው እየተጫወቱ ይገኛል።


40′ ጎል!!!!

ጃኮ አረፋት ያሻገረውን ኳስ ፍሬው ሰለሞን አሰቆጥሮ ሐዋሳን አቻ አድርጓል።


33′ ጎል!!!

ፍሬው ሰለሞን ያሻገረውን ኳስ ሀይማኖት ወርቁ አስቆጥሮ ልዩነቱን ማጥበብ ችሏል።


32′ ሀዋሳ ከተማ በፍሬው ሰለሞን አማኝነት ግብ ቢያስቆጥርም ከጨዋታ ውጭ አቋቋም ላይ ስለነበረ ግቡ ተሽሯል።


28′ ጎል!!!!

ፀጋዬ ብርሀኑ ያሻማውን ኳስ ቶማስ ስምረቱ በግንባሩ አስቆጥሮ የዲቻን ግብ ወደ ሁለት ከፍ አደረገ።


24′ ጎል!!!!

ፀጋዬ ብርሀኑ ከመስመር አክርሮ የመታውን ኳስ መላኩ ወልዴ ሊያወጣው ቢሞክርም ኳሱ በራሱ መረብ ላይ አርፎ ለዲቻ የመጀመሪያ ግብ ሆኖ ተቆጥሯል።


18′ አላዛር ፋሲካ ፀጋዬ ብርሀኑ ከመስመር ያሻገረውን ኳስ አግኝቶ ቢመታም ከግቡ አናት በላይ ወጥቶበታል።


17′ ጃኮ አረፋት ከፍሬው ሰለሞን ድንቅ ኳስ አግኝቶ ዳግም ሳይጠቀምበት ቀረ።


13′ ጃኮ አረፋት አሁንም ከግብ ጠባቂው ወንደሰን ጋር ተገናኝቶ ሐዋሳ ከተማን መሪ ሊያደርግ የሚችል ግልፅ የግብ ዕድል አመከነ።


10′ ሐዋሳ ከተማ የመጀመሪያውን ግብ ለማስቆጠር ጫና ፈጥሮ እየተጫወተ ይገኛል፡፡


4′ ጃኮ አረፋት ከርቀት አክርሮ የመታውን ኳስ ወንደወሰን ገረመው በአስደናቂ ሁሄታ አውጥቶታል።


1′ ጨዋታው እንደተጀመረ ጃኮ አረፋት ከኤፍሬም ዘካሪያስ የተሻገረው ኳስ ላይ በመድረስ አንድ ለአንድ ከግብ ጠባቂው ጋር ተገናኝቶ ቢሞክርም ኳሱ የግቡን ቋሚ ታኮ ወጥቷል።


1′ ጨዋታው በሐዋሳ ከተማ አማካይነት ተጀመረ።


8:43 – ይህን  ጫወታ ኢንተርናሽናል ዳኛ ለሚ ንጉሴ በዋና ዳኝነት፣ ፌድራል ዳኞች ጌቱ ተጫነ እና ሶርሳ ዱጉማ በረዳትነት፣ እንዲሁም ፌድራል ዳኛ ሰለሞን ዘገዬ በአራተኛ ዳኛነት በጋራ ይመሩታል። ሀይለመላክ ተሰማ የጨዋታው ኮሚሽነር ናቸው፡፡


8:35 – የሁለቱ ክለብ ተጫዋቾች ወደ ሜዳ ገብተው እያሟሟቁ ነው። የወላይታ ድቻ ደጋፊዎች በትሪብኑ በኩል የማያቋርጥ ድጋፍ እያደረጉም ይገኛሉ።የመጀመሪያ አሰላለፍ – ሐዋሳ ከተማ

1 አላዛር መርኔ

22 መላኩ ወልዴ

13 መሣይ ፓውሎስ

26 ወንድማገኝ ማህረግፈ

12 ደስታ ዩሀንስ

24 ሀይማኖት ወርቁ

25 ታፈሰ ሰለሞን

3 ኤፍሬም ዘካሪያስ

10 ፍሬው ሰለሞን

17 መድሀኔ ታደሰ

15 አረፋት ጃኮ


ተጠባባቂዎች

29 መክብብ ደገፉ

23 ፍርድአወቅ ሲሳይ

9 እስራኤል እሸቱ

4 አስጨናቂ ሉቃስ

2 ነጋሸ ታደሰ

20 ዮናታን ገዙ

19 ወንድሜነህ አይናለም


የመጀመሪያ አሠላለፍ – ወላይታ ዲቻ

1 ወንደሰን ገረመው

6 ተክሉ ታፈሰ

27 ሙባረክ ሽኩር

3 ቶማስ ስምረቱ

21 መሣይ አጪሶ

4 ዩሴፍ ድንገቶ

5 ዳግም ንጉሴ

23 ፀጋዬ  ብርሀኑ

17 በዛብህ መለዩ

19 አላዛር ፋሲካ

13 ዳግም በቀለ


ተጠባባቂዎች

12 ወንደሰን አሸናፊ

14 ሲሳይ ማም

2 ፈቱዲን ጀማል

8 አማኑኤል ተሾመ

20 አብዱልሰመድ አሊ

9 ያሬድ ዳዊት

10 እንዳለ መለዮ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
ያጋሩ

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

error: Content is protected !!