ሙገር ሲሚንቶ ከ ኢትዮጵያ ቡና

ቀን ፡ እሁድ የካቲት 2 ቀን 2006 አም.

ስታዲየም ፡ ደራርቱ ቱሉ ስታዲየም

የጨዋታ መጀመርያ ሰአት – 9፡00

በደረጃ ሰንጠረዡ ወገብ በ1 ነጥብ ተበላልጠው የተቀመጡት ሁለቱ ክለቦች አሰላ ላይ ይፋለማሉ፡፡ ጨዋታው ለኢትዮጵያ ቡና አስፈላጊ የመሆኑን ያህል ፈታኝ ይሆንበታል ተብሎ ይጠበቅበታል፡፡ አሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው በሲቲ ካፕ 3ኛ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀው ወጣት ቡድን እድገት እና በቻን የተሳተፉት ተጫዋቾች መመለስ ቡድናቸውን ከቀዝቃዛው የውድድር ዘመናቸው ለማነቃቃት አስተዋፅኦ ያበረክትላቸዋል፡፡

ጠቃሚ ነጥቦች

ሙገር 7ኛ ደረጃን ይዞ አደገኞቹን ሲያስተናግድ ኢትዮጵያ ቡና 9ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ ጨዋታውን ያደርጋል፡፡

ኢትዮጵያ ቡና ወደ አሰላ በሚያደርገው ጉዞ ብዙም ፈታና አይገጠመውም፡፡ በሊጉ እስካሁን ሙገር ኢትዮጵያ ቡናን 14 ጊዜ አስተናግዶ ያሸነፈው በ2 አጋጣሚዎች ብቻ ነው፡፡

የእርስ በእርስ ግንኙነቶች

ተጫወቱ – 28

ሙገር ሲሚንቶ አሸነፈ – 5

አቻ – 7

ኢትዮጵያ ቡና አሸነፈ – 16

ሙገር ሲሚንቶ አስቆጠረ – 22

ኢትዮጵያ ቡና አስቆጠረ – 44

{jcomments on}

ያጋሩ