ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ድሬዳዋ ከተማ | ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

FTቅዱስ ጊዮርጊስ3-0ድሬዳዋ ከተማ


30′ አዳነ ግርማ ፣ 67′ ሳላዲን ሰኢድ ፣ 83′ አብዱልከሪም ንኪማ


ተጠናቀቀ!!!
ጨዋታው በቅዱስ ጊዮርጊስ 3-0 አሸናፊን ተጠናቋል፡፡


ተጨማሪ ደቂቃ – 4


ጎልልል!!!
83′ አብዱልከሪም ንኪማ የቅዱስ ጊዮርጊስን መሪነት ወደ 3 አስፍቷል፡፡


79′ ከማዕዘን የተሻማውን ኳስ ፉአድ በግምባሩ ገጭቶ ቢሞክርም አስቻለው እና ግብ ጠባቂው ፍሬው መልሰውታል፡፡


የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
77′ ዘካርያስ ቱጂ ወጥቶ ምንያህል ተሾመ ገብቷል፡፡


የተጫዋች ለውጥ – ድሬዳዋ ከተማ
76′ ዘነበ ከበደ ወጥቶ ተስፋዬ ሃይሶ ገብቷል፡፡


የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
75′ አዳነ ግርማ ወጥቶ ራምኬል ሎክ ገብቷል፡፡


የተጫዋች ለውጥ – ድሬዳዋ ከተማ
73′ ረመዳን ናስር ወጥቶ ፉአድ ኢብራሂም ገብቷል፡፡


70′ ሳላዲን ሰኢድ የመታው ቅጣት ምት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡


ጎልልል!!!
67′ ሳላዲን ሰኢድ ከደጉ ደበበ የተሻገረለትን ኳስ ተቆጣጥሮ በግሩም ሁኔታ ወደ ግብነት ቀይሮታል፡፡


56′ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች በተቀናጀ ህብረ ዜማ ቡድናቸውን እየበረታቱ ይገኛሉ፡፡


52′ ሳላዲን ሰኢድ የመታውን ኳስ ግብ ጠባቂው ሲመልሰው አዳነ ግርማ ቢሞክርም ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡


ቢጫ ካርድ
51′ አቡበከር ሳኒ አስመስለህ ወድቀሃል በሚል የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡


49′ ከመስመር የተሻገረው ኳስ በተከላካዮች ሲመለስ ይሁን እንደሻው አየር ላይ እንዳለ በግሩም ቮሊ ወደ ግብ የመታውን ኳስ ፍሬው ይዞበታል፡፡


ተጀመረ!
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀመረ!


የእረፍት ሰአት ለውጥ
ቅዱስ ጊዮርጊስ | ሳላዲን በርጊቾ ወጥቶ ፍሬዘር ካሳ ገብቷል፡፡
ድሬዳዋ ከተማ | ዘላለም ኢሳያስ ወጥቶ ይሁን እንዳሻው ገብቷል፡፡
እረፍት!
የመጀመሪያው አጋማሽ በቅዱስ ጊዮርጊስ መሪነት ተጠናቋል፡፡


ተጨማሪ ደቂቃ – 2


44′ ምንተስኖት አዳነ ከሳጥን ውጪ የመታው ኳስ ኢላማውን ሳይጠብቅ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡


40′ ረመዳን ናስር የመታውን ቅጣት ምት ፍሬው በቀላሉ ይዞታል፡፡


34′ ሀብታሙ ወልዴ የመታውን ቅጣት ምት ፍሴው ጌታሁን አውጥቶታል፡፡


ጎልልል!!!! ቅዱስ ጊዮርጊስ
30′ አበባው ቡታቆ የመታው ቅጣት ምት የግቡን አግዳሚ ለትሞ ሲመለስ በቅርብ ርቀት የነበረው አዳነ ግርማ አግኝቶት ወደ ግብነት ቀይሮታል፡፡


25′ ከማዕዘን ምት የተሻማውን ኳስ በድጋሚ ምንተስኖት ገጭቶ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡


23′ ምንተስኖት አዳነ ከማዕዘን ምት የተሻማውን ኳስ በግምባሩ ገጭቶ ሳምሶን ይዞበታል፡፡


22′ ኢላማውን በጠበቀ የግብ ሙከራ ባይታጀብም ፈጣን እንቅስቃሴ እየታየበት ይገኛል፡፡


15′ ሳላዲን ሰኢድ በግብ ጠባቂው አናት የሰደደው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡


11′ ዘካርያስ ቱጂ ከመስመር ያሻገረለትን ጥሩ ኳስ ሳላዲን ሳይደርስበት ቀርቷል፡፡


4′ ሀብታሙ ወልዴ ከግቡ በቅርብ ርቀት ያገኘውን ኳስ በግቡ አናት ወደ ላይ ሰዶታል፡፡ የሚያስቆጭ አጋጣሚ!


ተጀመረ
ጨዋታው በድሬዳዋ ከተማ አማካኝነት ተጀምሯል፡፡


ሁለቱም ቡድኖች አሟሙቀው ወደ መልበሻ ክፍለ አምርተዋል፡፡


የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰላለፍ

1 ፍሬው ጌታሁን

15 አስቻለው ታመነ – 13 ሳላሀዲን ባርጊቾ – 12 ደጉ ደበበ (አምበል) – 4 አበባዉ ቡጣቆ

23 ምንተስኖት አዳነ – 27 አብዱልከሪም ኒኪማ

20 ዘካርያስ ቱጂ – 19 አዳነ ግርማ – 18 አቡበከር ሳኒ

7 ሳላዲን ሰኢድ


ተጠባባቂዎች
22 ዘሪሁን ታደለ
3 መሀሪ መና
2 ፍሬዘር ካሳ
24 ያስር ሙገርዋ
14 ምንያህል ተሾመ
25 አንዳርጋቸው ይላቅ
10 ራምኬል ሎክየድሬዳዋ ከተማ አሰላለፍ

1. ሳምሶን አሰፋ

2. ዘነበ ከበደ – 4. ተስፋዬ ዲባባ (አምበል) – 15 በረከት ሳሙኤል – 14. ኄኖክ አዱኛ

7 ሱራፌል ዳንኤል — 25. ዘላለም ኢሳይያስ — 23 አልሳአሪ አልማሃዲ — 10 ረመዳን ናስር

18. በረከት ይስሀቅ — 16. ሀብታሙ ወልዴ


ተጠባባቂዎች

71. ወርቅነህ ዲባባ
5 ዘሪሁን አንሼቦ
6 ይሁን እንዳሻው
9 አብዱ መሃመድ
17. ፉአድ ሀባስ
21 ያሬድ ታደሰ
13. ተስፋዬ ሀይሶ

1 Comment

Leave a Reply