አርባምንጭ ከነማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ

ቀን ፡ እሁድ የካቲት 2 ቀን 2006 አም.

ስታዲየም ፡ አርባምንጭ ስታዲየም

የጨዋታ መጀመርያ ሰአት – 9፡00

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በዚህ ሳምንት ሲጀመር የሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ አርባምንጭ ተጉዞ ጨዋታውን ያደርጋል፡፡ አሰልጣኝ ማርት ኑይ ከቻን እና ጉዳት መልስ ተጫዋቾቻቸው የተሟሉላቸው ሲሆን ማሸነፍ የሊጉን መሪነት በነጥብ ልዩነት እንዲይዙ ያደርጋቸዋል፡፡

የውድድር ዘመኑን ቀዝቅዞ የጀመረው አርባምንጭ ከነማ ሊጉ ከመቋረጡ በፉት በመልካም አቋም ላይ የነበረ ቢሆንም የውድድሩ ለ40 ቀናት ተቋርጦ መቆየት እያንሰራራ ለነበረው አርባምንጭ እክል ይፈጥራል፡፡ በሊጉ ሊሰናበቱ ከሚችሉ አሰልጣኞች አንዱ ለሆነው አሰልጣኝ አለማየሁ ይህን ጨዋታ ማሸነፍ ሲደርስበት የቆየውን ተቃውሞ ጋብ ያደርግለታል፡፡

ከቅዱስ ጊዮርጊስ በኩል በድንቅ አቋም ላይ የሚገኘው አጥቂው ፍፁም ገብረማርያም የውድድር ዘመኑ የመጀመርያ የሊግ ጨዋታውን እንደሚያደርግ ሲጠበቅ የኮከብ ግብ አግቢነት ፉክክሩን በ6 ግብ የሚመራው ኡመድ ኡኩሪን ቀድሞ በቋሚ አሰላለፍ ውስጥ ሊገባ ይችላል፡፡

ጠቃሚ ነጥቦች

ቅዱስ ጊዮርጊስ በሊጉ አናት ላይ ተቀምጦ ጨወታውን ሲያደርግ አርባምንጭ ከቅዱስ ጊዮርጊስ በ7 ነጥቦች አንሶ 6ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

አርባምንጭ ከነማ በ2004 ወደ ሊጉ ካደገ ወዲህ ቅዱስ ጊዮርጊስን አንድም ጊዜ ማሸነፍ አልቻለም፡፡

አርባምንጭ ከነማ ያለፉትን 5 ተከታታይ የሜዳ ላይ ጨዋታዎች እልተሸነፈም፡፡ በአንፃሩ ቅዱስ ጊዮርጊስ ባለፉት 15 ተከታታይ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋዎች ምንም ሽንፈት አልደረሰበትም፡፡

የእርስ በእርስ ግንኙነቶች

ተጫወቱ – 4

አርባምንጭ ከነማ አሸነፈ – 0

አቻ – 1

ቅዱስ ጊዮርጊስ አሸነፈ – 3

{jcomments on}

ያጋሩ