አርባምንጭ ከተማ 1-1 ደደቢት | የአሰልጣኞች አስተያየት 

ዻውሎስ ጸጋዬ – አርባምንጭ ከተማ

ስለ ጨዋታው

በመጀመርያው አጋማሽ ጥሩ አልነበርንም፡፡ በሁለተኛው አጋማሽ ላይ ግን በሚገባ ኳሱን ተቆጣጥረን ተጭነን ለመጫወት ሞክረናል፡፡ ተሳክቶልን ጎል አስቆጥረንም ነበር፡፡ ሆኖም ማሸነፍ እየተገባን በርካታ ያለቀለት ኳስ በመሳታችን አቻ ልንወጣ ችለናል። ”

የተጨዋቾች መዳከም

” ልጆቼ ከ70 ደቂቃ በኋላ በተወሰነ መልኩ ተዳክመው ነበር፡፡ ያም የተጓዝነው ረጅም ርቀት አዳክሞን ነው፡፡ ከአአ -ድሬደዋ – አርባምንጭ ያውም በመኪና… ፡፡ ይሄ በልጆቹ ላይ ከፍተኛ  አሉታዊ ተፅዕኖ ነበረው፡፡”

 

የአጨራረስ ድክመት

” እንደሚታወቀው ምርጥ የሆኑ የአጥቂ አማካዮች ያሉበት ስብስብ ነው፡፡ የጎል ዕድልም ይፈጥራሉ ፤ ሆኖም የአጥቂዎቻችን የአጨራረስ አቅም ድክመት ዋጋ እያስከፈለን ቢሆንም በቀጣይ አስተካክለን እንቀርባለን፡፡”

አስራት ኃይሌ – ደደቢት

ስለ ጨዋታው

” ከአአ ወጥተን እንደ መጫወታችን መጠን ውጤቱ ለእኛ ጥሩ ነው ። አንደኛ ሜዳው ለጨዋታ ፈፅሞ አመቺ አይደለም ፤ ሁለተኛ አየሩ ከባድ ነበር ፤ ሦስተኛ ቁልፍ ተጨዋቾቻችንን አስራት መገርሳ ፣ ሳምሶን ጥላሁን ፣ ስዩም ተስፋዬን በጉዳት ይዘን አለመምጣታችን ጎድቶናል፡፡ አብዛኛዎቹ ተቀያሪ ወንበር ላይ የነበሩት ከታዳጊ የመጡ ናቸው፡፡ ይህ ሁሉ ተደማምሮ ይህን ነጥብ ይዞ መውጣት ትልቅ ውጤት ነው። ”

 

ከሜዳ ውጭ አለማሸነፍ

” እርግጥ ነው ከሜዳ ውጭ አላሸነፍንም፡፡ ያም ሆኖ በሶስት ከሜዳ ውጭ ጨዋታዎች አልተሸነፍንም ፤ ይሄም ጥንካሬ ነው፡፡ ያው ከሜዳ ውጭ እንደመጫወታችን ነጥብ ተጋርቶ መውጣትን እንደ ማሸነፍ እንቆጥረዋለን ”

 

የጌታነህ የአጨራረስ ብቃት

” እሱ የተለየ አጥቂ ነው፡፡ አቋቋሙ ፣ እይታው ፣  በየትኛውም አጋጣሚ የጎል የማግባት አጋጣሚ የመፍጠር ችሎታው እና ወደ ጎልነት የመቀየር ብቃቱ ልዩ ነው፡፡ በሊጉም ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ነው፡፡ እኔ የምችለው ስለ እርሱን ማድነቅ ብቻ ነው፡፡”

Leave a Reply