ቅዱስ ጊዮርጊስ 3-0 ድሬዳዋ ከተማ | የአሰልጣኞች አስተያየት

ማርት ኖይ – ቅዱስ ጊዮርጊስ

“ሁላችንም ከቡናው ጨዋታ መከፋት በኃላ ማሸነፍ ፍላጎት ነበረን፡፡ ከሊቀ-መንበሩ እስከ የሜዳ ሰራተኛው ማሸነፍ ፍላጎት ነበረን፡፡ የመጀመሪያ ግብን በፍጥነት ለማግኘት አልመን ነበር ፤ ለዚህም ኳስ ስናገኝ ጫና ፈጥረናል፡፡ በመስመር፣ በተሸጋሪ ኮሶች እና ወደ የፍፁም ቅጣት ምቱ ሰብሮ በመግባት ሞክረናል፡፡ ዕድል ከእኛ ጋር ነበረች፡፡ የአበባውን ቅጣት ምት አዳነ በግንባሩ አስቆጥሯል፡፡

” ለእኔ ጨዋታው እንደሌሎቹ ጨዋታዎች ነው፡፡ እስካሁን 9 ጨዋታዎችን ተጫውተናል፡፡ የተለየ ልዩነት በጨዋታዎች መካከል አላየሁም፡፡ በአብዛኛው የተሻልን ነበርን፡፡ አንዳንድ ግዜ ግብ ለማስቆጠር ትንሽ እድለኛ መሆን ነበረብን፡፡ አንዳንድ ግዜ እድለኛው ተቃራኒ ቡድን ነበር፡፡ ይህ እግርኳስ ነው፡፡

ዘላለም ሽፈራው – ድሬዳዋ ከተማ

“ጨዋታው በጣም ጠንካራ ነበር፡፡ ምክንያቱም ሁለታችንም ከሽንፈት ማግስት ነው የመጣነው፡፡ ስለዚህ ክፍት ነበር ታክቲካሊ የተዘጋ ነገር አልነበረውም፡፡ ሁለታችንም ውጤቱን እንፈልገው ስለነበር ጨዋታው ክፍት ነበር፡፡ ጊዮርጊስም ዛሬ በጣም ጥሩ ነው፡፡ እንቅስቃሴያቸው በጣም ጥሩ ነው የነበረው፡፡  የእኛ ደግሞ በተቃራኒ ከአጋማሹ ወደፊት ያለው የመሃል ክፍላችንም እና ከፊት ያለው የአጥቂ ክፍላችንም ጥሩ አልነበረም፡፡ ይህ ዋጋ አስከፍሎናል፡፡ ”

ቀጣይ ጨዋታችን ከደደቢት ነው፡፡ ደደቢት ደግሞ የሚታወቅ ነው የሊጉ አናት ላይ ካሉ ክለቦች መካከል አንዱ ነው፡፡ በሜዳችን ነው ጨዋታውን የምናደርገው፡፡ ቢሆንም ባለፈው ሳምንት በሜዳችን ተሸንፈናል፡፡ ስለዚህ አሁንም በጣም ስራ እንደሚጠብቀን ግልፅ ነው፡፡ ምክንያቱም ነጥቦችን ሰብስበን ከአደጋው ዞን መውጣት ስላለብን ለዚህም ከፊት ላለው የደደቢት ጨዋታ ለሌሎችም ጨዋታዎች ጠንክረን እንቀርባለን፡፡”

Leave a Reply