የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እሁድ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይጀመራል

በብሄራዊ ቡድኑ የቻን ዝግጅት ለ40ቀናት ያህል ተቋርጦ የነበረው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በ10ኛ ሳምንት እሁድ እና ሰኞ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይጀመራል፡፡ ስድስቱንም ጨዋታ አሸንፎ በደረጃ ሰንጠረዡ አናት ላይ የተቀመጠው ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ አርባምንጭ ተጉዞ አርባምንጭ ከነማን ይጎበኛል፡፡ የቡድኑ ተጫዋቾች ከቻን መልስ በማገገማቸው ለጨዋታ ብቁ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በአንፃሩ አርባምንጭ ከነማዎች ከውድድሮች ርቀው መቆየታቸው በአእምሮ እና በአካል ብቃቱ በኩል ተዳክመው ሊመጡ ይችላሉ፡፡

በ9ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ኢትዮጵያ ቡና ወደ አሰላ አቅንቶ ሙገር ሲሚንቶን ይገጥማል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ላይ የተካፈሉት ሁለቱ ቡድኖች እሁድ በ9 ሰአት በደራርቱ ቱሉ ስታዲየም ይጫወታሉ፡፡

በሊጉ ግርጌ ላይ የሚገኙት ዳሸን ቢራ እና መብራት ኃይል በፋሲለደስ ስታዲየም 9 ሰአት ላይ ይጫወታሉ፡፡ እስካሁን ምንም ግብ ያላስቆጠረው ዳሸን ቢራ እና እድግ ተዳክሞ የቀረበው መብራት ኃይል ከአደጋው ዞን ለመውጣት የግድ ይህንን ጨዋታ ማሸነፍ አለባቸው፡፡

ሀረር ላይ ሐረር ቢራ ሲዳማ ቡናን የሚያስተንግድበት ጨዋታም በሳምንቱ መጨረሻ ከሚካሄዱ ጨዋዎች አንዱ ሲሆን የክለቦቹን የውድድር አመት እጣ ፈንታ የሚወስን ወሳኝ ጨዋታ ነው፡፡

ሰኞ በብቸኝነት በሚደረገው ጨዋታ የአዲስ አበባ ዋንጫ የፍፃሜ ተፋላሚው ኢትዮጵያ መድን ወላይታ ዲቻን ያስተናግዳል፡፡በአዲስ አበባ በርካታ ደጋፊዎች ያሉት ወላይታ ዲቻ ከ6 ተከታታይ ጨዋዎች የአቻ ውጤት አገግሞ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ፤ ቀስ በቀስ ወደ ውድድር ሪትም እየገባ ያለው መድንም ከዋረጅ ቀጠናው ለመራቅ ሰኞ በ11 ሰአት ይጫወታሉ፡፡

{jcomments on}