ወንድሜነህ ዘሪሁን አዳማ ከነማን ተቀላቀለ

በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ኤሌከትሪክን የተቀላቀለው ወነድሜነህ ዘሪሁን ክለቡን ለቆ ወደ አዳማ ከነማ ማምራቱ ተነግሯል፡፡

የአጥቂ አማካዩ በኤሌክትሪክ መደላደል የተሳነው ሲሆን አሰልጣኝ አጥናፉ አባተ በተደጋጋሚ ቀይረው ሲያስወጡትም ተስተውሏል፡፡ በዚህም ከአሰልጣኙ ጋር ግጭት ውስጥ በመግባቱ ክለቡን መልቀቁ ታውቋል፡፡

አሰልጣኝ አጥናፉ ከወንድሜነህ በተጨማሪ ከዮርዳኖስ አባይ ጋር በፈጠሩት ግጭት አጥቂው ከክለቡ ጋር መለያየቱ የሚታወስ ነው፡፡

አዳማ ከነማ በውድድር ዘመኑ አጋማሽ የዝውውር መስኮት ሌላውን የቀድሞ የኤሌክትሪክ አጥቂ ዮናታን ከበደን ከዳሽን ቢራ አስፈርሟል፡፡

በተያያዘ ዜና የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና አምበል ከወልድያ ጋር ልምምድ ሲሰራ ቆይቶ ለክለቡ ሳይፈርም መቅረቱ ታውቋል፡፡ አማካዩ ስሙ ከወልድያ ተጫዋች/አሰልጣኝነት ስራ ጋር ስሙ ተያይዞ ነበር፡፡

ያጋሩ