የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሊጠናቀቅ 4 ተስተካካይ ጨዋታዎች ብቻ ይቀራሉ፡፡
በ10ኛው ሳምንት መካሄድ የነበረበት የደደቢት እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ፍልሚያ ሰማያዊዎቹ ጦረኞች በአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ምክንያት ባለመካሄዱ ነገ ይጫወታሉ፡፡
ከ12 ጨዋታዎች አስራ አንዱን አሸንፎ በ33 ነጥቦች የሊጉን አናት ላይ የተቀመጠው ቅዱስ ጊዮርጊስ የ1ኛ ዙር የመጨረሻ ጨዋታውን ሲያደርግ ደደቢት በበኩሉ ከነገው ጨዋታ ቀጥሎ ባሉት 10 ቀናት ውስጥ ቀሪዎቹን 2 ተስተካካይ ጨዋታዎች ያደርጋል፡፡
የአምናው ሻምፒዮን ደደቢት ዘንድሮ ከደረጃው እጅግ የወረደ ቡድን ይዞ ሲቀርብ ቅዱስ ጊዮርጊስ በበኩሉ በሁሉም ቦታዎች የተሟላ ስብስብ ይዞ አብዛኛዎቹን ጨዋታዎች በቀላሉ አሸንፏል፡፡ በርካቶች የነገው ጨዋታ አሸናፊነትን ከወቅታዊ አቋማቸው በመነሳት ለቅዱስ ጊዮርጊስ የሰጡ ሲሆን የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎችም የአምና ቁጭታቸውን ለመወጣት ቡድናቸው ዝግዱ እንደሆነ በተለያዩ መንገዶች እየገለፁ ይገኛል፡፡ ደደቢቶችም ይህንን ጨዋታ ማሸነፍ ለቀሪ ለተቀዛቀዘው የሊግ ጉዟቸው ትልቅ መነሳሻ ይሆንላቸዋል፡፡
በጨዋታው በሁለቱም ቡድኖች በኩል የቀድሞ ክለባቸውን ለመጀመርያ ጊዜ ለመግጠም የተዘጋጁ ተጫዋቾች መኖራቸው ትኩረትን ስቧል፡፡ አምና ከቅዱስ ጊዮርጊስ ወጣት ቡድን አድጎ ለዋናው ቡድን ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ ሲያሳይ የነበረው አማካዩ ሳምሶን ጥላሁን በነገው ጨዋታ የደደቢትን ማልያን ለብሶ ፈረሰኞቹን ይፋለማል፡፡ በተመሳሳይ በቅዱስ ጊዮርጊስ ለ4 አመታት የቆየው መስፍን ኪዳኔ በደደቢት ማልያ የቀድሞ ክለቡን ይገጥማል፡፡ አምና ለደደቢት ሻምፒዮንነት ቁልፍ ሚና የተጫወቱት በኃይሉ አሰፋ እና ምንያህል ተሾመ በፈረሰኞቹ በኩል የቀድሞ ክለባቸውን የቀድሞ ክለባቸውን የሚገጥሙ ናቸው፡፡
{jcomments on}