FTመከላከያ1-2አርባምንጭ ከ.
78′ ሳሙኤል ታዬ | 36′ ጸጋዬ አበራ 41′ ገብረሚካኤል ያዕቆብ
ተጠናቀቀ !!!
ጨዋታው በአርባምንጭ ከተማ አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
ተጨማሪ ደቂቃ – 5
86′ ካርሎስ ዳምጠው ከግቡ በቅርብ ርቀት ተንሸራቶ የመታው ኳስ ወደ ውጨጪ ወጥቷል፡፡ መከላከያ ጫና በመፍጠር ላይ ይገኛሉ፡፡
ጎልልል!!!!
78′ ሳሙኤል ታዬ መከላከያ ያገኘውን ቅጣት ምት መትቶ በግሩም ሁኔታ አስቆጥሯል፡፡ 1-2
የተጫዋች ለውጥ – መከላከያ
76′ ሽመልስ ተገኝ ወጥቶ ካርሎስ ዳምጠው ገብቷል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – መከላከያ
68′ የተሻ ግዛው ወጥቶ ተመስገን ገብረጻዲቅ ገብቷል፡፡
66′ በመስመር በኩል ከታደለ የተሻገረለትን ኳስ ገብረሚካኤል በቀጥታ ወደ ግብ መትቶ መረቡን ታኮ ወጥቷል፡፡
63′ ታደለ መንገሻ በመልሶ ማጥቃት እንቅስቃሴ ከጸጋዬ የተሻገረለትን ኳስ ሞክሮ በግቡ አናት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡ አርባምንጮች በፈጣን መልሶ ማጥቃት የመከላከያ ተከላካዮችን እየፈተኑ ይገኛሉ፡፡
59′ ተካልኝ ደጀኔ ያሻማውን ቅጣት ምት አለልኝ አዘነ በግምባሩ ገጭቶ ቢሞክርም አቤል ማሞ ይዞበታል፡፡
51′ ማራኪ ወርቁ በአርባምንጭ የፍጹም ቅጣት ምት ሳጥን ውስጥ በተደጋጋሚ ኳሶች ቢያገኝም መጠቀም አልቻለም፡፡
49′ የተሻ ግዛው ከሳጥኑ ጠርዝ የሞከረውን ኳስ አንተነህ መሳ ይዞበታል፡፡
ተጀመረ
2ኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀመረ!
እረፍት !!!
የመጀመርያው አጋማሽ በእንግዶቹ 2-0 መሪነት ተጠናቋል፡፡
ተጨማሪ ደቂቃ – 3
ጎልልል!!!!
42′ ገብረሚካኤል ያዕቆብ የፍጹም ቅጣት ምቱን ወደ ግብነት ቀይሮታል 2-0
ፍጹም ቅጣት ምት – አርባምንጭ
41′ ገብረሚካኤል ያዕቆብ ብ ጠባቂውን አልፎ ወደ ግብ ሊመታ ሲል በአዲሱ ተስፋይ ተጠልፎ የፍጹም ቅጣት ምት ተሰጥቷል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – አርባምንጭ
38′ አምበሉ አማኑኤል ጎበና (ጉዳት) ወጥቶ አለልኝ አዘነ ገብቷል፡፡
ጎልልል!!!!
36′ ከቅጣት ምት የተሻገረውን ኳስ ጸጋዬ አበራ ወደ ግብነት ቀይሯታል፡፡
35′ አማኑኤል ጎበና የማዕዘን ምት ሲሻማ ግጭት ደርሶበት ከባድ ጉዳት አስተናግዷል፡፡
30′ ጨዋታው በሙከራ ባይታጀብም ፈጣን እንቅስቃሴ እየታየበት ይገኛል፡፡
24 በጥሩ የመልሶ ማጥቃት የሄደውን ኳስ አማኑኤል ጎበና ሞክሮ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡
19′ ከመስመር የተሻገረውን ኳስ በሃይሉ ግርማ ሞክሮ አንተነህ አውጥቶበታል፡፡ ግሩም ሙከራ!
ቢጫ ካርድ
18′ ወንድሜነህ ዘሪሁን የጨዋታውን የመጀመርያ ማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡
17′ የአርባምንጭ ደጋፊዎች ዳኛው በሚወስናቸው ውሳኔዎች ብስጭታቸውን እየገለፁ ይገኛሉ፡፡
13′ ወንድሜነህ ዘሪሁን ከርቀት የሞከረው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡
10′ መከላከያ ፈጣን የማጥቃት እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡
5′ ከየተሻ ግዛው የተሻገረውን ኳስ ማራኪ ሞክሮ አንድነት አዳነ ከግቡ መስመር አውጥቶታል፡፡
ተጀመረ
ጨዋታው በመከላከያ አማካኝነት ተጀምሯል፡፡
የመጀመሪያ አሠላለፍ – መከላከያ
1 አቤል ማሞ
2 ሽመልስ ተገኝ – 16 አዲሱ ተስፋዬ – 17 ምንተስኖት ከበደ – 3 ቴዎድሮስ በቀለ –
19 ሳሙኤል ታዬ – 21 በሀይሉ ግርማ – 13 ሚካኤል ደስታ – 9 ሳሙኤል ሳሊሶ
7 ማራኪ ወርቁ – 10 የተሻ ግዛው
የመጀመሪያ አሰላለፍ – አርባምንጭ
1 አንተነህ መሳ
2 ተካልኝ ደጀኔ – 5 አንድነት አዳነ – 16 በረከት ቦጋለ – 14 ወርቅይታደል አበበ
10 ወንድሜነህ ዘሪሁን – 4 ምንተስኖት አበራ – 8 አማኑኤል ጎበና -17 ታደለ መንገሻ
22 ጸጋዬ አበራ – 19 ገብረሚካኤል ያዕቆብ