ኢትዮጵያ ቡና ከ ሀዋሳ ከተማ | ቀጥታ የጽሁፍ ስርጭት

FTኢት. ቡና2-1ሀዋሳ ከተማ

7′ አስቻለው ግርማ, 23′ ጋቶች ፓኖም | 60′ ደስታ ዮሀሃንስ


ተጠናቀቀ!!!
ጨዋታው በኢትዮጵያ ቡና አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

90+5′ ሳዲቅ ሴቾ የመታው የፍጹም ቅጣት ምት የግቡን ቋመሚ ገጭቶ ወጥቷል፡፡

ፍጹም ቅጣት ምት !
አስቻለው ግርማ ግብ ጠባቂውን ለማለፍ ሲሞክር በመጠለፉ የፍጹም ቅጣት ምት ተሰጥቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ቡና
90+3′ ያቡን ዊልያም ወጥቶ ሳዲቅ ሴቾ ገብቷል፡፡

90+1′ ጋቶች ፓኖም ከርቀት የሞከረውን ኳስ ሜንሳህ ይዞበታል፡፡

ቢጫ ካርድ
90+1′ አስናቀ ሞገስ ኳስ በማዘግየት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ – 5

የተጫዋች ለውጥ – ሀዋሳ
88′ ዳንኤል ደርቤ ወጥቶ ፍርዳወቅ ሲሳይ ገብቷል፡፡

85′ አማኑኤል በግብ ጠባቂው አናት የሰደደውን ኳስ ወንድማገኝ አውጥቶታል፡፡ ኳሷ የግብ መስመሩን አልፋለች በሚል የቡና ደጋፊዎች እና ተጫዋቾች ቅሬታቸውን በማሰማት ላይ ይገኛሉ፡፡ በጋቶች ፓኖም አማካኝነት ቡናዎች ክስ በማስመዝገብ ላይ ይገኛሉ፡፡

80′ ሀዋሳ ከተማዎች የአቻነት ግብ ለማግኘት ጫና ፈጥረው እየተጫወቱ ይገኛሉ፡፡ ሙሉ ለሙሉ የኳስ ቁጥጥር ብልጫም ወስደዋል፡፡

75′ ዳንኤል ደርቤ ከመስመር ያሻገረውን ኳስ ደስታ ዮሃንስ ሳይደርስበት ቀርቷል፡፡ የሚያስቆጭ አጋጣሚ!

የተጫዋች ለውጥ – ቡና
73′ አብዱልከሪም ሀሰን ወጥቶ አክሊሉ ዋለልኝ ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ሀዋሳ
69′ መድሃኔ ታደሰ ወጥቶ ታፈሰ ሰለሞን ገብቷል፡፡

62′ አማኑኤል ዮሃንስ ከሳጥን ውስጥ የመታውን ኳስ ሜንሳህ አውጥቶበታል፡፡

ጎልልል!!!!
60′ ከቅጣት ምት የተሻማውን ኳስ ደስታ ዮሃንስ አስቆጥሯል፡፡ 2-1

የተጫዋች ለውጥ – ሀዋሳ
55′ ኃይማኖት ወርቁ ወጥቶ ወንድማገኝ ማዕረግ ገብቷል፡፡

53′ አማኑኤል ያቡን ዊልያምን ከግብ ጠባቂው ጋር አንድ ለአንድ ተገናኝቶት የሞከረው ኳስ የግቡን አግዳሚ ለትሞ ወጥቷል፡፡

49′ መድሃኔ ታደሰ የሞከረው ኳስ በተከላካዮች ተደርቦ ወጥቷል፡፡

ተጀመረ!!
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡


እረፍት
የመጀመሪያው አጋማሽ በቡና መሪነት ተጠናቋል፡፡

ቢጫ ካርድ
41′ ሜንሳህ ሶሆሆ ኳስ በድጋሚ እንዳይጀመር በማገድ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመዞበታል፡፡

40′ የቡና ደጋፊዎች የአህመድ ረሺድን ስም እየጠሩ በመዘመር ላይ ይገኛሉ፡፡

39′ ከቅጣት ምት የተሻገረውን ኳስ ወንድይፍራው በግምባሩ በመግጨት ሞክሮ ለጥቂት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

30′ ጃኮ አራፋት አክርሮ የመታውን ቅጣተት ምት ሀሪሰን አውጥቶታል፡፡

ቢጫ ካርድ
30′ ወንድይፍራው ጌታሁን የማስጠንቀቂያ ካርደድ ተመልክቷል፡፡

26′ ጋዲሳ መብራቴ የመታው ቅጣት ምት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

ጎልልል!!!!
23′ ፍጹም ቅጣት ምቱን ጋቶች ፓኖም ግብ ጠባቂውን በተቃራኒ አቅጣጫ በመስደድ አስቆጥሯል፡፡

22′ አስቻለው ግርማ በአስገራሚ ፍጥነት ወደ ፍጹም ቅጣተት ምተት ሲገባ በመጠለፉ የፍጹም ቅጣት ምት ተሰጥቷል፡፡

19′ ከመስመር የተሻገረውን ኳስ መድሃኔ ተንሸራቶ ሞክሮ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡

15′ ኤፍሬም ዘካርያስ የሞከረውን ኳስ ሀሪሰን ሲመልሰው ዘካርያስ በድጋሚ አግኝቶ ሞክሮ ተከላካዮች አውጥተውታል፡፡

15′ ሁለቱም ወደ ግብ በፍጥነት ለመድረስ እየጣሩ ይገኛሉ፡፡ ነገር ግን አጥቂዎቹ በጨዋታ ውጪ አቋቋም እየተገኙ ነው፡፡

ጎልልል!!!!
7′ አስቻለው ግርማ ከእያሱ ታምሩ የተሻገረለትን ኳስ በአግባቡ ተቆጣጥሮ ኢትዮጵያ ቡናን ቀዳሚ አድርጓል፡፡

ተጀመረ!
ጨዋታው በሀዋሳ ከተማ አማካኝነት ተጀምሯል፡፡

የኢትዮጽያ ቡና አሰላለፍ

99 ሀሪሰን ሄሱ

18 ሣለአምላክ ተገኝ – 16 ኤፍሬም ወንድወሰን – ወንድይፍራው ጌታሁን – 21 አስናቀ ሞገስ

17 አብዱልከሪም ሀሰን – 25 ጋቶች ፓኖም – 8 አማኑኤል ዮሐንስ

24 አስቻለው ግርማ  – 28 ያቡን ዊልያም – 14 እያሱ ታምሩ

የሀዋሳ ከተማ አሰላለፍ 

 1.ሶሆሆ ሜንሳ

7 ዳንኤል ደርቤ – 13 መሳይ ጳውሎስ – 22 መላኩ ወልዴ – 12 ደስታ ዮሀንስ

24.ሀይማኖት ወርቁ – 3 ኤፍሬም ዘካርያስ– 10.ፍሬው ሰለሞን  

17 መድሃኔ ታደሰ – 15 ጃኮ አራፋት – 11 ጋዲሳ መብራቴ

Leave a Reply