ሉሲዎቹ ነገ ከናሚቢያ ጋር የወዳጅነት ጨዋታቸውን ያደርጋሉ

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ለአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ለማለፍ ከጋና ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ ዝግጅት ከጀመረ ሳምንት ተቆጥሯል፡፡

በቀድሞው የወንዶች ብሄራዊ ቡድን ምክትል አሰልጣኝ ስዩም ከበደ የሚመራው የሴቶች ብሄራዊ ቡድን ነገ ከናሚቢያ ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ 23 ተጫዋቾችን ይዞ ወደ ዊንድሆክ አምርቷል፡፡

የወዳጅነት ጨዋታው ነገ 11፡00 ላይ የሚጀምር ሲሆን ተጫዋቾቹም ዛሬ 9፡00 ላይ በሚጫወቱበት ስታዲየም ልምምድ እንዳደረጉ ታውቋል፡፡

የሉሲዎቹ ተጫዋቾች እና አሰልጣኞች ወደ ስፍራው ከማምራታቸው በፊት ከኤቲቪ ጋር ባደረጉት ቆይታ በወዳጅነት ጨዋታው እና አጠቃላይ የሴቶች እግርኳስ ላይ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ ዋና አሰልጣኙ ስዩም ከበደ ፌዴሬሽኑ የወዳጅነት ጨዋታዎች በመጀጋጀታቸው መደሰታቸውን ገልፀው የወጣት እና ታዳጊ ሴቶች የውስጥ ውድድሮች በማዘጋጀት የበለጠ ትኩረት እንዲያደርግ መክረዋል፡፡ የብሄራዊ ቡድኗ አምበል ብዙሃን እንዳለ በበኩሏ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ በመጀመሩ የተሻለ ለውድድሮች ብቁ እንዳደረጋቸው ገልፃለች፡፡ በቡድኑ ተጫዋቾች ላይ ያለው የቡድን ህብረት እና ብቃት እየተሸሻለ እንደመጣ የገለፁት ደግሞ ምክትል አሰልጣኙ ብርሃኑ ግዛው ናቸው፡፡

{jcomments on}

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *