አዲሱ የብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሰኞ ይፋ እንደሚሆን ይጠበቃል

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አዲሱ አሰልጣኝ በይፋ የሚገለፅበት ቀን እየራቀ ሃገሪቱም ካለ ብሄራዊ ቡድን 2 ወራትን አስቆጥራለች፡፡ ከፌዴሬሽኑ የሚወጡ ጭምጭምታዎች እንደሚያመለክቱት ግን ፌዴሬሽኑ ምርጫውን እንደጨረሰና ጎራን ስቴፋኖቪች በአሰልጣኝነት እንደተሾሙ እየተነገረ ነው፡፡

ፌዴሬሽኑ ከ27 አመልካቾች ውስጥ የመጨረሻ 5 እጩዎችን መለየቱን ተከትሎ አርብ እለት የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ይታወቃል ተብሎ ቢጠበቅም የቴክኒክ ኮሚቴው ከ5ቱ እጩዎች ጋር ሊያደርግ ያሰበው የስካይፒ ቃለመጠይቅ በኢንተርኔት ኔትዎርክ ችግር ምክንያት ተራዝሟል፡፡

አሰልጣኞቹን የመምረጥ ሃላፊነት የተሰጠው የቴክኒክ ኮሚቴው በመጀመርያ ካመለከቱት 27 አሰልጣኞች 10ሩን ቀጥሎን 10ሩን ኋላ ላይ ደግሞ 5ቱን ያስቀሩ ሲሆን አሰልጣኝ ዲዬጎ ጋርዚያቶ ከ5 እጩዎች ወጥተው አሁን ለመጨረሻ እጩነት የቀረቡት አሰልጣኞች ቁጥር 4 ደርሷል፡፡ የደሞዝ ድርድር ከተካሄደ በኋላ የሚመረጠው አሰልጣኝም ሰኞ ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

{jcomments on}

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *