መብራት ኃይል አዩላ ሞሰስን አስፈረመ

በውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኘው መብራት ኃይል ናይጄርያውን የአጥቂ አማካይ አዩላ ሞሰስ አስፈርሟል፡፡

‹‹ ካኑ ›› በሚለው ቅፅል ስሙ የሚታወቀው አዩላ ኒያላን የተቀላቀለው በ2004 ከሌላው የኢትዮጵያ ክለብ ድሬዳዋ ከነማ ሲሆን ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣቱ ቀደም ብሎ በናይጄርያ ዋናው እና ዝቅተኛ ዲቪዥን ለፕሌቱ ዩናይትድ ፣ ፕራይም ፣ ኒጀር ቶርናዶስ እና ክራውን ክለቦች ከ2005 እስከ 2011 ድረስ ተጫውቷል፡፡ በልደታ ኒያላ እና ድሬዳዋ ከነማ በቆየባቸው 2 አመት ከ6 ወራት አብዛኛው ጊዜውን ያሳለፈው በብሄራዊ ሊግ በመጫወት ነው፡፡

አዩላ በአንድ ወቅት ከአንድ ከናይጄርያ ሚድያ ጋር ባደረገው ቆይታ ናይጄርያዊ በመሆኑ ብቻ ከሱ ብዙ ተአምር እንደሚጠበቅ መናገሩ ይታወሳል፡፡ ‹‹ የውጭ ዜጋ ከሆንክ ከኢትዮጵያውያን በላይ እንድትጫወት ይጠበቅብሃል፡፡ የውጭ ተጫዋች ሁሉ በሜሲ ደረጃ ላይ ያለ ይመስላቸዋል፡፡ ›› ብሎ ነበር፡፡

በአጥቂ አማካይነት እና አጥቂነት መጫወት የሚችለው አዩላ በመብራት ኃይል ከ2ኛው ዙር ጀምሮ መጫወት የሚችል ሲሆን የቅርብ ጓደኛው አዎኒዪ ሚካኤል በቡድኑ በመገኘቱ የማይዘሙት ምሶሶዎችን በፍጥነት ይላመዳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

{jcomments on}

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *