ካሜሮን 2019፡ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ተጋጣሚዎቿን አውቃለች

በ2017 የቶታል አፍሪካ ዋንጫ አዘጋጅ በሆነችው ጋቦን ርዕሰ መዲና ሊበርቪል የ2019 የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ድልድል ይፋ ሆኗል፡፡ ኢትዮጵያ በምድብ ስድስት ከጋና፣ ሴራሊዮን እና ጎረቤት ኬንያ ጋር ተደልድላለች፡፡ 

ኢትዮጵያ በ2013 ለአፍሪካ ዋንጫ ካለፈች በኃላ ወደ ታላቁ የአህጉሪቱ ውድድር መመለስ ከብዷታል፡፡ ኢትዮጵያ ወደ 2019 የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የግድ ጋናን፣ ኬንያን እና ሴራሊዮንን መርታት ይጠበቅባታል፡፡ ጋና በ2017 የአፍሪካ ዋንጫ የምትሳተፍ ሲሆን ከ2008 ጀምሮ ይበልጥ ተጠናክራ መጥታለች፡፡ ምዕራብ አፍሪካዊቷ ሴራሊዮን በእግርኳሱ እምብዛም ባትታወቅም በ2015 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከሱዳን በተሻለ ኮትዲቯርን መፈተን ችላለች፡፡ ኬንያ አስቀድሞ ከአፍሪካ ዋንጫው መውደቋን ብታረጋግጥም የኮንጎ ብራዛቪል የአፍሪካ ዋንጫ ህልም አጨናግፋለች፡፡ ኬንያ ከ2004 ወዲህ አፍሪካ ዋንጫ ላይ ተሳትፋ አታውቅም፡፡

ኢትዮጵያ እና ኬንያ ለመጨረሻ ግዜ በቻን ማጣሪያ ተገናኝተው ኢትዮጵያ በአጠቃላይ ውጤት 2-0 ማሸነፏ ይታወሳል፡፡ ይህ በእንዲ እንዳለ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታዎች መጋቢት 2017 የሚደረጉ ይሆናል፡፡

1 Comment

Leave a Reply