የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2ኛ ዙር ሚያዝያ 8 ይጀመራል

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2ኛው ዙር ጨዋታ ሚያዝያ 4 ቀን 2006 አም. እንደሚጀመር የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የውድድር እና ስነስርአት ኮሚቴ አስታውቋል፡፡

ህዳር 16 የጀመረው የዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በብሄራዊ ቡድን ዝግጅት ፣ በቻን አፍሪካ ዋንጫ እና በአፍሪካ የክለብ ውድድሮች ምክንያት ሲንጠባጠብ ቆይቶ 1ኛው ዙር ሊጠናቀቅ 3 ጨዋታዎች ብቻ ቀርተዋል፡፡ አርባምንጭ ከነማ ፣ ሙገር ሲሚንቶ ፣ ዳሸን ቢራ እና ኢትዮጵያ መድን የአንደኛው ዙር መርሃ ግብራቸውን በሙሉ አጠናቀው ቀደም ብለው እረፍት ሲያደርጉ ደደቢት እና ወላይታ ድቻ መጋቢት 29 ፣ ኢትዮጵያ ቡና ደግሞ መጋቢት 24 የ1ኛ ዙር ጨዋታቸውን ያጠናቅቃሉ፡፡

ፕሪሚየር ሊጉ በመርሃ ግብር በኩል ሁሉንም ክለቦች ያማከለ ባለመሆኑ አንዳንድ ክለቦች ላይ ተፅእኖ መፍጠሩ የማይቀር ነው፡፡ በተከታታይ በተስተካካይ ጨዋዎች የተጠመደው ደደቢት የ1ኛውን ዙር ካጠናቀቀ ከ5 ቀናት በኋላ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር የ14ኛውን ሳምንት ጨዋታ ሲያደርግ ከ1 ወር የበለጠ ጊዜ አረፍት ያደረጉ እንደ አርባምንጭ እና ሙገር ያሉ ክለቦች በተጠራቀመ ጉልበት 2ኛውን ዙር ይጀምራሉ፡፡

የ2ኛው ዙር 14ኛ ሳምንት ጨዋታዎች የሚከተሉት ናቸው

ኢትዮጵያ ቡና ከ ደደቢት – አአ

አርባምንጭ ከነማ ከ ኢትዮጵያ መድን – አርባምንጭ

ሐረር ቢራ ከ ዳሽን ቢራ – ሐረር

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ሙገር ሲሚንቶ – አአ

ወላይታ ድቻ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ – ቦዲቲ

ሲዳማ ቡና ከ መከላከያ – ይርጋለም

መብራት ኃይል ከ ሀዋሳ ከነማ

{jcomments on}

ያጋሩ