ደደቢት ከ መከላከያ | ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

FT ደደቢት 0-0 መከላከያ 


ጨዋታው ያለግብ 0-0 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል።


90+1′ የተጨዋች ለውጥ – መከላከያ

ሳሙኤል ታዬ ወጥቶ ካርሎስ ዳምጠው ገብቷል።


90′ ተጨማሪ ሰዐት – 5 ደቂቃ


89′ ስዩም ተስፋዬ ያሻማውን የማዕዘን ምት አክሊሉ አያነው በግንባሩ ሞክሮ አቤል ማሞ አውጥቶበታል።


88′ የተጨዋች ለውጥ – ደደቢት

አስራት መገርሳ ወጥቶ አቤል እንዳለ ገብቷል።


87′ የተጨዋች ለውጥ – ደደቢት

ሰለሞን ሐብቴ በጉዳት በወጣው ብርሀኑ ቦጋለ ምትክ ወደሜዳ ገብቷል።


86′ ብርሀኑ ቦጋለ በቃሬዛ ከሜዳ ወጥቷል ተመልካቹም በጭብጨባ አበረታቶታል።


84′ የሁለቱም ብድን ተጨዋቾች በተጎዳው ብርሀኑ ቦጋለ ዙሪያ ተሰብስበዋል። የህክምና እርዳታም እየተደረገለት ነው ።


82′ ሽመልስ ተገኝ ኳስ ከግብ ክልሉ ሲያርቅ ኳሱ ብርሀኑ ቦጋለ አንገት ላይ በማረፉ ተጨዋቹ ከባድ ጉዳት አስተናግዷል።


78′ ደደቢቶች በቀኝ መስመር ያገኙትን ቅጣት ምት ብርሀኑ ቦጋለ መቶት የመከላከያ ተጨዋቾች ካወጡት በኋላ በቴዎድሮስ ታፈሰ አማካይነት በግራ መስመር የሰነዘሩት ጥሩ መልሶ ማጥቃት ወደጎል ማግባት እድል ሳይቀየር ባክኖ ቀርቷል።


77′ የተጨዋች ለውጥ መከላከያ

ሚካኤል ደስታ ወጥቶ ኡጉታ ኦዶክ ገብቷል።


75′ ብርሀኑ ቦጋለ ከደደቢቶች ፍፁም ቅጣት ምት ክልል ውስጥ የሞከረው ኳስ በተከላካዮች ሲመለስ ድጋሚ ሞክሮ ወደላይ ተነስቶበታል።


73′ ከተጋጣሚያቸው የግብ ክልል ረጅም ርቀት ላይ እየተንቀሳቀሱ ያሉት ሁለቱ የደደቢት አጥቂዎች እስካሁን ጠንካራ የግብ ሙከራ ማድረግ አልቻሉም።


70′ ከቅያሪው በኋላ መከላከያዎች በሁለቱ መስመሮች እየገቡ ጫና ለመፍጠር እየሞከሩ ነው።


68′ የተጨዋች ለውጥ መከላከያ

ማራኪ ወርቁ ወጥቶ ቴውድሮስ ታፈሰ ገብቷል።


63′ ሽመክት ጉግሳ መሀል ሜዳ ላይ በማራኪ ወርቁ ላይ በሁለት እግሩ ሸርታቴ በመውረዱ ምክንያት ማራኪ ተጎድቶ ወድቆ የህክምና እርዳታ እየተደረገለት ነው። የመከላከያ አሰልጣኝ እና ተጨዋቾች ዳኛው ሁኔታውን በዝምታ በማለፋቸው ቅሬታቸውን ገልፀዋል።


61′ ሽመክት ጉግሳ ከቀኝ መስመር አክሮ የሞከረው ኳስ ወደውጪ ወጥቷል።


52′ ጨዋታው እንደመጀመሪያው አጋማሽ ሁሉ መቀዛቀዝ እየታየበት ነው ።


51′ አስራት መገርሳ በሳሙኤል ሳሊሶ ላይ በሰራው ጥፋት የቢጫ ካርድ ተመልክቷል።


50′ ጌታነህ ከበደ እና ሽመክት ጉግሳ በጥሩ ቅብብል ወደ መከላካዮች የፍፁም ቅጣት ምት ክልል ለመግባት ሞክረው አልተሳካላቸውም።


46′ ሁለተኛው አጋማሽ በደደቢቱ ጌታነህ ከበደ አማካይነት ተጀምሯል ።የመጀመሪያው አጋማሽ ግብ ሳይቆጠርበት 0-0 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል።


45′ ተጨማሪ ሰዐት – 2 ደቂቃ


44′ ሚካኤል ደስታ በግራ በኩል ያነሳውን የማዕዘን ምት አወል አብደላ በግንባሩ ሲሞክር ኳስ መሬት ላይ ነጥራ በግቡ አናት ወጥታለች።


40′ ደደቢቶች የኳስ ቁጥጥር የበላይነቱን እየወሰዱ ይገኛሉ፤ ግልፅ የማግባት አጋጣሚ ግን እየፈጠሩ አይደለም።


38′ ምንይሉ ወንድሙ ከሳሙኤል ታዬ ከመሀል ሜዳ የተሻገረለትን ኳስ ይዞ የደደቢትን ተከላካዮች እያለፈ እና ወደግራ እያሰፋ ሄዶ ወደ ውስጥ ለማሻማት ቢሞክርም ክሌመንት በቀላሉ ይዞበታል።


35′ በሂደት ደደቢቶች ወደ ተጋጣሚያቸው የሜዳ ክልል እየቀረቡ ይገኛሉ።


30′ ጨዋታው በተቀዛቀዘ ሁኔታ እየቀጠለ ነው። ደደቢቶች ይዘውት በገቡት የ 3-5-2 ቅርፅ በመሀል ሜዳ ላይ ሊኖራቸው ሚገባውን የበላይነት ማሳየት አልቻሉም። የመከላከያዎች የኳስ ቁጥጥር ብልጫም ወደ ተጋጣሚያቸው የሜዳ ክልል ማለፍ አልቻለም።


26′ ሳሙኤል ሳሊሶ ያሻማውን የማዕዘን ምት ምንይሉ ወንድሙ በግንባሩ ሞክሮ ለጥቂት ወደላይ ተነስቶበታል።


25′ ሚካኤል ደስታ ከቀኝ መስመር ያሻማውን ኳስ በሀይሉ ግርማ በግንባሩ ሞክሮ ተከላካዮች ተደርበው አውጥተውበታል።


22′ የጨዋታው የመጀመሪያ ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ!

የመከላከያው የፊት አጥቂ ምንይሉ ወንድሙ ከደደቢቶች ሳጥን ውጪ አክርሮ የሞከረውን ኳስ ክሌመንት አውጥቶበታል። ጨዋታው በማዕዘን ምት ቀጥሏል።


20′ ቴውድሮስ በቀለ ከ ስዩም ተስፍዬ ጋር መሀል ሜዳ አካባቢ ተጋጭቶ ቢወድቅም የህክምና እርዳታ ተደርጎለት ወደሜዳ ተመልሷል።


16′ የቅጣት ምቱን ከመከላከያዎች የፍፁም ቅጣት ምት ቀኝ ጠርዝ ላይ ጌታነህ ከበደ በቀጥታ ሞክሮ ወደላይ ወጥቶበታል።


15′ አዲሱ ተስፋዬ በፍፁም ቅጣት ምት ክልል መግቢያ ላይ ሽመክት ጉግሳን በመጎተቱ የቢጫ ካርድ ተመልክቷል።


10′ ከርቀት የተገኘውን የቅጣት ምት ብርሀኑ ቦጋለ ሲያሻማ ሽመክት ጉግሳ በግንባሩ ለማስቆጠር ሞክሮ ኳሷ ላይ ሳይደርስባት ቀርቷል።


6′ መከላከያዎች በመሀል ሜዳ እና በራሳቸው የሜዳ ክልል ላይ ኳስ ተቆጣጥረው በረጃጅም ኳሶች ወደ ደደቢት የግብ ክልል ለመድረስ እየሞከሩ ነው።


1′ ጨዋታው በመከላከያ አማካይነት ተጀምሯል።


የአዲስ አበባ ስቴድየም ውስጥ በየቦታው አልፎ አልፎ ተበታትነው ከሚታዩ ተመልካቾች በቀር የተቀዛቀዘ ድባብ ይታያል።


08፡55 – የሁለቱም ቡድኖች ተጨዋቾች አሟሙቀው ወደመልበሻ ክፍል ገብተዋል።


የመጀመሪያ አሰላለፍ – ደደቢት

33 ክሌመንት አሼቲ

 15 ደስታ ደሙ — 6 አይናለም ኃይለ — 14 አክሊሉ አየነው —  

7 ስዩም ተስፋዬ —  24 ካድር ኩሊባሊ — 4 አስራት መገርሳ — 19 ሽመክት ጉግሳ–10 ብርሀኑ ቦጋለ

 9 ጌታነህ ከበደ — 17 ዳዊት ፍቃዱ


ተጠባባቂዎች

22 ታሪክ ጌትነት

16 ሰለሞን ሀብቴ

27 እያሱ ተስፋዬ

18 አቤል እንዳለ

11 አቤል አያሌው

99 ያሬድ ብርሀኑ

25 ብርሀኑ አሻሞ


የመጀመሪያ አሰላለፍ – መከላከያ

1 አቤል ማሞ

3 ቴዎድሮስ በቀለ — 16 አዲሱ ተስፋዬ — 4 አወል አብደላህ — 2 ሽመልስ ተገኝ

19 ሳሙኤል ታዬ — 21 በሀይሉ ግርማ — 13 ሚካኤል ደስታ — 9. ሳሙኤል ሳሊሶ

7 ማራኪ ወርቁ — 14 ምንይሉ ወንድሙ


ተጠባባቂዎች

22 ይድነቃቸው ኪዳኔ

17 ምንተስኖት ከበደ

28 ሚሊዬን በየነ

15 ቴውድሮስ ታፈሰ

11 ካርሎስ ዳምጠው

10 የተሻ ግዛው

26 ኡጉታ ኦሎክ

Leave a Reply