ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ ወላይታ ድቻ | ቀጥታ የጽሁፍ ስርጭት

FT ኢትዮ ኤሌክትሪክ 2-1 ወላይታ ድቻ 

48′ አዲስ ነጋሽ፣ 75′ ፍፁም ገ/ማርያም || 81′ መሳይ አጪሶ


ጨዋታው በኤሌክትሪክ 2-1 አሸናፊነት ተጠናቀቀ። ኤሌክትሪክ የውድድር አመቱን የመጀመሪያ ድል አስመዝግቧል።


90+1 የተጨዋች ለውጥ – ኤሌክትሪክ

ፍፁም ገ/ማርያም ወጥቶ አቤል አክሊሉ ገብቷል።


90′ አላዛር ፋሲካ መሬት የወደቀውን ኢብራሂም ፍፋኖን ሰዐት እየገደል ነው ብሎ ለማንሳት ባረገው ጥረት ቢጫ ካርድ ተመልክቷል።


90′ ተጨማሪ ሰዐት – 5 ደቂቃ


89′ ኤሌክትሪኮች ውጤት ለማስጠብቅ አፈግፍገው በመልሶ ማጥቃት እየተጫወቱ ይገኛሉ።


87′ እንግዳው ቡድን በደጋፊዎቹ የማያባራ ድጋፍ ታጅቦ ከቆሙ ኳሶች በመነሳት የአቻነቷን ግብ ለማግኘት እየጣረ ነው።


82′ ፍፁም ገ/ማርያም ተጎድቶ በቃሬዛ ወጥትቷል። ሙባረክ ሽኩርም ጊዜ እየገደለ ነው በማለት በፈጠረው ሰጣገባ የቢጫ ካርድ ሰለባ ሆኗል።


81′ ጎል!!!

ወላይታ ድቻ በግምት ከ25 ሜትር ርቀት ላይ ያገኘውን ቅጣት ምት ተቀይሮ የገባው መሳይ አጪሶ በቀጥታ መትቶ በመጀመሪያ የኳስ ንክኪው ግብ አስቆጥሯል። ግሩም ግብ !


80′ የተጨዋች ለውጥ – ወላይታ ድቻ

ቴዎድሮስ መንገሻ እና መሳይ አጪሶ ገብተው አማኑኤል ተሾመ እና በዛብህ መለዮ ወጥተዋል።


75′ ጎል!!!

ኢብራሂም ፍፋኖ ከቀኝ መስመር ያሻገረለትን ኳስ በመጠቀም ፍፁም ገ/ማርያም ለኤሌክትሪክ ሁለተኛ ግብ አስቆጥሯል።

ኤሌክትሪክ በውድድር ዘመኑ ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድጨዋታ ከአንድ በላይ ጎል ማስቆጠር ችሏል።


72′ አማኑኤል ተሾመ በግምት ከ 30 ሜትር ላይ የተገኘውን ቅጣት ምት በቀጥታ መትቶ ግብ ጠባቂው ይዞበታል።


70′ አማኑኤል ተሾመ መሀል ሜዳ ላይ በሰራው ጥፋት ቢጫ ካርድ ተመልክቷል። የወላይታ ድቻ ተጨዋቾች እና ደጋፊዎች በዳኛው ውሳኔ ደስተኛ አልሆኑም።


68′ አልቢትሩ ፍፁም ገ/ማርያምን በፍፁም ቅጣት ምት ክልል ውስጥ አስመስለህ ወድቀሀል በማለት የቢጫ ካርድ አሳይተውታል ።


66′ ድቻዎች ሁለቱን መስመሮች በመጠቀም በተጋጣሚያቸው ላይ ጫና እየፈጠሩ ነው።


64′ ኢብራሂም ፍፋኖ በጉዳት ምክንያት ወድቆ የህክምና እርዳታ እየተደረገለት ነው። የድቻ ደጋፊዎች ሰዐት ለመግደል ነው በሚል ተቃውሟቸውን እያሰሙ ነው።


63′ የተጨዋች ለውጥ – ወላይታ ድቻ

ትክሉ ታፈሰ ወጥቶ ዳግም በቀለ ገብቷል።


60′ ከአማኑኤል ተሾመ ሙከራ በኋላ የድቻዎች ጫና በርትቷል። በስቴድየሙ በብዛት ሚገኙት የቡድኑ ደጋፊዎች ቡድናቸውን በከፍተኛ ሁኔታ እያበረታቱ ነው።


57′ አማኑኤል የሾመ በግምት ከ 28 ሜትር ርቀት ላይ አክርሮ የሞከረውን ኳስ ሱሊማን ኤቡ ወደውጪ አውጥቶበታል። ጨዋታው በማዕዘን ምት ቀጥሏል።


53′ አሁንም ኤሌክትሪኮች የተሻለ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፤ ነገር ግን ከኋላ ሚላኩ  ኳሶች የፊት አጥቂዎቹን እያገኙ አይደለም።


48′  ጎል!!!

አዲስ ነጋሽ የፍፁም ቅጣት ምቱን ወደግብነት ቀይሮታል።


47′ ፍፁም ቅጣት ምት ! 

በበሀይሉ ተሻገር ላይ በተሰራው ጥፋት ምክንያት ኤሌክትሪኮች ፍፁም ቅጣት ምት አግኝተዋል።


46′ የኤሌክትሪኩ  ኢብራሂም ፎፋኖ ሁለተኛውን የጨዋታ አጋማሽ አስጀምሯል።የመጀመሪያው አጋማሽ ያለግብ ተጠናቋል።


45′ ተጨማሪ ሰዐት – 1 ደቂቃ


41′ ፍፁም ገ/ማርያም በግራ መስመር ሁለት ተጨዋቾችን አልፎ የሰጠውን ኳስ ኢብራሂም ፍፋኖ ሲመልስለት ፍፁም በግራ እግሩ አክርሮ ቢሞክርም ኳሱ በግራ በኩል ወደላይ ወጥቶበታል።


39′ አወት ገ/ሚካኤል ከቀኝ መስመር ያሻማውን ኳስ አማኑኤል ተሾመ ለማውጣት ሲሞክር ለጥቂት በራሱ ግብ ላይ ሊያስቆጥር ነበር።


36′ እዛው ቦታ ላይ አማኑኤል ተሾመ በበሀይሉ ተሻገር ላይ ሌላ ጥፋት ሰርቶ  አሸናፊ ሽብሩ የተሰጠውን ቅጣት ምት ወደውስጥ ሲያሻማ እና ተከላካዮች በግንባራቸው ሲያወጡት የፍፁም ቅጣት ምት ሳጥን ጠርዝ ላይ የነበረው አዲስ ነጋሽ በቀጥታ አክርሮ ሞክሮ ለጥቂት ወደላይ ወጥቶበታል። ግሩም ሙከራ !


35′ በድቻዎች የፍፁም ቅጣት ምት ጠርዝ ላይ በዋለልኝ ገብሬ ላይ የተሰራውን ጥፋት ተከትሎ የተሰጠውን ቅጣት ምት አሸናፊ ሽብሮ መቶት ወደላይ ተነስቶበታል።


32 ‘ ወንደሰን አሸናፊ ኳስ ከጎሉ ለማራቅ ሲሞክር ፍፁም ገ/ማርያም ተደርቦበት የነበረ ቢሆንም ፍፁም አጋጣሚውን ወደጎል ከመቀየሩ በፊት ወንደሰን ይዞበታል።


29′ ተስፋዬ መላኩ ከግራ መስመር ለጎል የመታው ኳስ ዋለልኝ ገብሬ ጋር ደርሶ ዋለልኝ ከ ድቻዎች ሳጥን ውስጥ ተረጋግቶ ሞክሮ ለጥቂት በጎሉ ጎን ወትቶበታል።


27′ ኤሌክትሪኮች መሀል ሜዳ ላይ ኳስ ቢይዙም ከኋላ አምስት የተከላካይ መስመር ተጨዋቾች በተጨማሪም ሌላ የአራት ተጨዋቾች አጥር የሰራውን የድቻን አማካይ ክፍል ማለፍ አልቻሉም።


25′ ኢብራሂም ፍፋኖ በሜዳው አጋማሽ ግራ መስመር ላይ በአናጋው ባድግ ላይ በሰራው ጥፋት የጨዋታውን የመጀመሪያ ቢጫ ካርድ ተመልክቷል።


23′ በጥሩ መልሶ ማጥቃት አላዛር ፋሲካ ከበዛብህ መለዮ የተላከለትን ኳስ ተቀብሎ ወደ ውስጥ ቢያሻማም ሱሊማን ኤቡ አውጥቶበታል።


18′ ከሜዳው አጋማሽ በጥቂቱ ወደፊት ጠጋ ብሎ የተገኘውን ቅጣት ምት አማኑኤል ተሾመ ሲያሻማ አሸናፊ ሽብሩ በግንባሩ ጨርፎ አውጥቶበታል ። ጨዋታው በማዕዘን ምት ቀጥሏል።


15′ ወላይታ ድቻዎች በራሳቸው የሜዳ ክልል ላይ በጥልቀት በመከላከል በመልሶ ማጥቃት ወደግብ ለመሄድ እየሞከሩ ነው።


11′ ኤሌክትሪኮች በተጋጣሚያቸው ሜዳ ላይ ከፍተኛ ጫና ፈጥረው እየተጫወቱ ነው ።


7′ ፍፁም ገ/ማርያም ከመሀል ያሻገረለትን ኳስ ኢብራሂም ፍፋኖ አገባው ተብሎ ሲጠበቅ የሞከረውን ኳስ ወንደሰን አሸናፊ አውጥቶበታል። ጨዋታው በማዕዘን ምት ቀጥሏል።


3′ ጨዋታው ፈጠን ባለ እንቅስቃሴ በወላይታ ድቻዎች የድጋፍ ድባብ ታጅቦ ተጀምሯል።


1′ ጨዋታው በወላይታ ድቻ አማካይነት ተጀምሯል።


የመጀመሪያ አሰላለፍ – ኢትዮ ኤሌክትሪክ

22 ሱሊማን አቡ
2 አወት ገ/ሚካኤል – 21 በረከት ተሰማ – 5 አዲስ ነጋሽ – 15 ተስፋዬ መላኩ 

8 በሀይሉ ተሻገር – 23  አሸናፊ ሽብሩ – 9 ብሩክ አየለ – 24 ዋለልኝ ገብሬ

16 ፍፁም ገ/ማርያም – 4  ሒብራሂም ፎፋኖ


ተጠባባቂዎች

1 ኦኛ ኦሜኛ

7 አለምነህ ግርማ

13 ሲሳይ ብርሀኑ

11 አቤል አክሊሉ

14 ስንታየው ሰለሞን

17 አብዱልሀኪም ሱልጣን

12 ትዕዛዙ መንግስቱ


የመጀመሪያ አሰላለፍ – ወላይታ ድቻ 

1 ወንድወሰን አሸናፊ

27  ሙባረክ ሽኩር – 3 ቶማስ ስምረቱ – 11 ተክሉ ታፈሰ

2 ፈቱዲን ጀማል – 4 ዮሴፍ ድንገቶ – 8 አማኑኤል ተሾመ –  23 ፀጋዬ ብርሀኑ

17 በዛብህ መለዮ – 19 አላዛር ፋሲካ– 7 አናጋው ባደግ


ተጠባባቂዎች

12 ወንድወሰን ገረመው

5 ዳግም በቀለ

28 መሳይ አጪሶ

20 አብዱልሰመድ አሊ

16 ቴውድሮስ መንገሻ

13 ዳግም በቀ

10 እንዳለ መለዮ

Leave a Reply