‹‹ አሁንም የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ እኔ ነኝ ›› ማርያኖ ባሬቶ

ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣንነታቸው እንደተነሱ እየተወራባቸው የሚገኙት አሰልጣኝ ማርያኖ ባሬቶ ከተወዳጁ ጨዋታ የሬድዮ ፕሮግራም ጋር ባደረጉት ቆይታ ከብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝነታቸው ስለመነሳታቸው የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ተናግረዋል፡፡

‹‹ ከአሰልጣኝነት መባረር ማለት ምን ማለት ነው// እኔ ለፈረንጆች ፋሲካ በአል ወደ ሃገሬ መመለሴን እንጂ መሰናበቴን አላውቅም፡፡ አሁንም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ እኔ ነኝ ›› ብለዋል፡፡

ፌዴሬሽኑ አሰልጣኙ ስለመነሳታቸው ይፋዊ መግለጫ እስካሁን አልሰጠም፡፡

ያጋሩ