ደደቢት ከአፍሪካ ኮንፌድሬሽን ዋንጫ ውጪ ሆነ

በአፍሪካ ኮንፌድሬሽንስ ዋንጫ ደደቢት ዛሬ በባህርዳር ስታድየም ባደረገው የመልስ ጨዋታ ከዋሪ ዎልቭስ ጋር ካለ ግብ አቻ በመለያየት ከውድድሩ አንደኛ ዙር ተሰናብቷል፡፡

በመጀመርያው ጨዋታ 2-0 ተሸንፎ የተመለሰው ደደቢት በጨዋታው ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ቢያደርግም የናይጄርያውን ክለብ ግብ ሳይደፍር ጨዋታው ካለግብ ተጠናቋል፡፡

በተለይም በመጀመርያዎቹ 20 ደቂቃዎች ደደቢቶች ጫና ፈጥረው መንቀሳቀስ የቻሉ ሲሆን በዋሪው ግብ ጠባቂ ግብ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡

ደደቢት ለ3ኛ ጊዜ ከአንደኛ ዙር ለማለፍ ያደረገው ጥረት ዘንድሮም ሳይሳካ ቀርቷል፡፡

 

ያጋሩ