የኤሲሚላን ታዳጊ ኢትዮጵያውያንና ጥቁሮች የዘረኝነት ጥቃት ደረሰባቸው

የኤሲ ሚላን ከ10 አመት በታች ታዳጊዎች ቡድን ልጆቻቸውን ሊመለከቱ በመጡ ወላጆች የዘረኝነት ጥቃት ደርሶባቸዋል፡፡

ጣልያን ውስጥ በተዘጋጀ ውድድር ላይ የኤሲ ሚላን ከ10 አመት በታች ቡድን የፈረንሳዩ ፒ.ኤስ.ጂ አቻውን 4-0 ባሸነፈበት ጨዋታ 2 ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የማሊ እና ሴኔጋል ተወለ፤ጆች ላይ የዘረኝነት ስድቦች አስተናግደዋል፡፡

ኤሲሚላን ስለ ዘረኝነት ጥቃቱ ማረጋገጫ የሰጠ ሲሆን ዝነኛው የተጫዋቾች ወኪል ሚኖ ራዮላም በጥቃቱ የተሰማውን ብስጭት በትዊተር ገፁ ገልጧል፡፡

‹‹ የ10 አመት ህናት ሲሰደቡ ማየት በጣም ያስደነግጣል፡፡ ነገር ግን አንገታችሁን ቀና አድርጉ እኛ ከነዛ ደካማ ዘረኞች በላይ ጠንካሮች ነን ›› ሲል ሚኖ ራዮላ ገልጧል፡፡

48 ታላላቅ የአውሮፓ ክለቦች በተሳተፉበት ውድድር አሰግድ ኢቫን እና አበበ ሉስቼቲ የሚገኙበት ኤሲ ሚላን ለግማሽ ፍፃሜ ደርሷል፡፡

ከዚህ ቀደም በኤሲ ሚላን የተጫወተው ጋናዊ ኬቪን ፕሪንስ ቦአቴንግ ተመሳሳይ የዘረኝነት ጥቃት ማስተናገዱ አይዘነጋም፡፡

ያጋሩ