ፋሲል ከተማ ከ ደደቢት | ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

FTፋሲል ከተማ0-1ደደቢት

84′ ሽመክት ጉግሳ


ተጠናቀቀ !!
ጨዋታው በእንግዳው ደደቢት 1-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ – 4

የተጨዋች ለውጥ ደደቢት
87′ ታደለ ባይሳ ወጥቶ ሙሉቀን ታሪኩ ገብቷል፡፡

ጎልልል!!!! ደደቢት!
84″ ሽመክት ጉግሳ ከኤፍሬም አሸሞ የተሻገረለትን ወደ ጎልነት ቀይሮታል፡፡

83’ደደቢት የአቻ ውጤቱን አስጠብቆ ለመውጣት አፄዎቹ ጎል ለማስቆጠር ከፍተኛ ፉክክር እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

ቢጫ ካርድ
78′ ኩሊባሊ ካድር የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

የተጨዋች ለውጥ – ፋሲል ከተማ
76′ ናትናኤል ጋንጂላ ገብቶ ኤርሚያስ ኃይሉ ገብቷል፡፡

ቢጫ ካርድ
74′ ኄኖክ ገምቴሳ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

የተጨዋች ለውጥ – ደደቢት
71′ ተቀይሮ የገባው አቤል አያሌው ወጥቶ ጌታነህ ከበደ ገብቷል፡፡

ቢጫ ካርድ
69′ ክሌመንት ሰአት በማባክን የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

66′ አፄዎቹ በተደጋጋሚ ወደ ጎል ለመቅረብ ጥረት ቢያደርጉም ጠንካራ የሆነውን የደደቢት ተከላካዮች ሰብረው መግባት አልቻሉም፡፡

የተጨዋች ለውጥ – ፋሲል ከተማ
62′ ሰለሞን ገ/መድህን ገብቶ ኤፍሬም አለሙ ወጥቷል፡፡

56′ ጨዋታው በሁለቱም በኩል በሚታይ ፈጣን እንቅስቃሴ ተሟሙቆ እየቀጠለ ይገኛል፡፡

ቢጫ ካርድ
54′ ደስታ ደሙ ኳስ በእጁ በማስቀረቱ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

ቢጫ ካርድ
50′ ኤፍሬም አለሙ ኳስ በእጁ በመንካቱ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

የተጨዋች ለውጥ – ደደቢት
ሳምሶን ጥላሁን ገብቶ አቤል እንዳለ ወጥቷል፡፡

ተጀመረ!
2ኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡


እረፍት!
የመጀመርያው አጋማሽ ያለ ግብ ተጠናቋል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ – 1

42′ አቤል አያሌው ከግብ ጠባቂው ጋር አንድ ለአንድ ተገናኝቶ ሳተው፡፡

40′ አብዱራህማን በግራ እግሩ አክሮ የመታውን ኳስ ክሌመንት እንደምንም ተወርውሮ ወደ ውጭ አወጣው፡፡ አስደናቂ ሙከራ!

የተጨዋች ለውጥ – ደደቢት
ዳዊት ፍቃዱ ወቶ አቤል አያሌው ገብቷል፡፡

36′ ሽመክት ጉግሳ ከቀኝ መስመር የተሻገረለትን ኳስ በግሩም ሁኔታ መትቶ አግዳሚውን ታኮ ወጣ፡፡

30′ የፋሲል ደጋፊዎች እና ተጨዋቾች የፍፁም ቅጣት ምት ሊሰጠን ይገባ ነበር በማለት ዕለቱን ዳኛ እየተቃወሙ ይገኛሉ፡፡

24′ በግምት ከ18 ሜትር ርቀት የተሰጠውን ቅጣት ምት ኤፍሬም አሻሞ መትቶ ምንተስኖት አድጎ በሚገርም ሁኔታ አድኖበታል፡፡

22′ በሁለቱም ቡድኖች በኩል ተመጣጣኝ የሆነ የጨዋታ እንቅስቃሴ እየተመለከትን እንገኛለን፡፡

11′ ኄኖክ ገምቴሳ ከግራ መስመር ያሻገረውን ቅጣት ምት ኤርሚያስ ሀይሉ በግንባሩ ገጭቶ ለጥቂት ወጣበት፡፡

7′ ፋሲል ከተማዎች ምንም እንኳ የተሳካ የጎል ሙከራ ባያደርጉም በተደጋጋሚ ወደ ጎል በመድረስ ከደደቢት የተሻለ እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

ተጀመረ!
ጨዋታው በፋሲል አማካኝነት ተጀመረ፡፡

09:00 የጎንደር ከተማ ከንቲባ አቶ ተቀባ ተባበል ተጫዋቾችን እየተዋወቁ ይገኛሉ፡፡

08:45 ሁለቱም ቡድኖች አሟሙቀው ወደ መልበሻ ክፍልአምርተዋል 

08:40 የሊጉ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ጌተታነህ ከበደ በአስገራሚ ሁኔታ ከመጀመርያው አሰላለፍ ውጪ ሆኗል፡፡  

08:30 ሜዳው በተመልካች ተሞልቷል፡፡ እጅግ አስደናቂ ድባብ እየታየበትም ይገኛል፡፡

የፋሲል ከተማ አሰላለፍ

1 ምንተስኖት አድጎ

7 ፍጹም ከበደ –  5 ታደለ ባይሳ – 16 ያሬድ ባየህ– 21 አምሳሉ ጥላሁን

17 ይስሃቅ መኩርያ – 26 ሄኖክ ገምተሳ – 6 ኤፍሬም አለሙ

99 ኤርምያስ ሃይሉ – 9 ኤዶም ሆሮሶውቪ – 18 አብዱራህማን ሙባረክ

ተጠባባቂዎች

31 ቴዎድሮስ ጌትነት
10 ሙሉቀን ታሪኩ
24 ያሬድ ዝናቡ
14 ከድር ኸይረዲን
4 ፍቅረሚካኤል አለሙ
27 ሰለሞን ገብረመድህን
20 ናትናኤል ጋንጂላ

የደደቢት አሰላለፍ
33 ክሌመንት አዞንቶ

7 ስዩም ተስፋዬ – 6 አይናለም ኃይለ – 14 አክሊሉ አየነው – 15 ደስታ ደሙ

24 ካድር ኩሊባሊ – 4 አስራት መገርሳ – 18 አቤል እንዳለ

19 ሽመክት ጉግሳ – 17 ዳዊት ፍቃዱ – 21 ኤፍሬም አሻሞ

ተጠባባቂዎች
22 ታሪክ ጌትነት
11 አቤል ያለው
8 ሳምሶን ጥላሁን
16 ሰለሞን ሐብቴ
27 እያሱ ተስፋዬ
9 ጌታነህ ከበደ
25 ብርሃኑ አሻሞ

Leave a Reply