AFCON 2017 ፡ ኢትዮጵያ አልጄርያን በድጋሚ ትገጥማለች

የ2017 አፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ድልድል ዛሬ ይፋ ሆኗል፡፡ የካፍ ፅህፈት ቤት በሚገኝበት ካይሮ በተካሄደው ስነስርአት በቋት 2 ውስጥ የነበረችው ኢትዮጵያ በምድብ 10 ከአልጄርያ ፣ ሌሴቶ እና ሲሸልስ ጋር ተደልድላለች፡፡ ከዚህ መድብ 1ኛ ሆኖ የሚያጠናቅቀው ቡድን በቀጥታ ወደ አፍሪካ ዋንጫው ሲያልፍ 2ኛ ሆኖ የሚያጠናቅቀው ቡድን በሌሎች ምድቦች ሁለተኛ ሆነው ካጠናቀቁት ቡድኖች የተሸለ ውጤት ካስመዘገበ ወደ 31ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የሚያልፍ ይሆናል፡፡

ኢትዮጵያ እና አልጄርያ ባለፈው አመት (2014) ለ30ኛው የአፍሪከ ዋንጫ ማጣርያ በአንድ ምድብ ተገናኝተው አልጄርያ ሁለቱንም ጨዋታዎች ማሸነፏ አይዘነጋም፡፡

ዛሬ ከምድብ ድልድሉ በፊት በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የአፍሪካ ዋንጫ አስተናጋጅ ሃገር ማንነት ይፋ የሆነ ሲሆን ጋቦን ለውድድር የቀረቡት ጋና እና አልጄርያን በመብለጥ የ2017 የአፍሪካ ዋንጫን እንድታዘጋጅ ተመርጣለች፡፡

ያጋሩ