FTቅዱስ ጊዮርጊስ 1-1ጅማ አባ ቡና
69′ ሳልሀዲን ሰይድ 36′ ኪዳኔ አሰፋ
የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ተቃውሞ ቀጥሏል። የጅማ አባ ቡናው አሰልጣኝ ደረጄ በላይ በሜዳው ለተገኙት የ ጅማ አባ ቡና ደጋፊዎች የስንብት ሚመስል ሰላምታ ሰጥተዋል።
ጨዋታው በ 1 – 1 ውጤት ፍፃሜውን አግኝቷል።
90+4 አዳነ ግርማ ከመሀል የተሻገረውን እና ሳልሀዲን ያልደረሰበትን ኳስ በቅርብ ርቀት አግኝቶ ቢሞክርም ሙላት ይዞበታል።
90+3 ቅዱስ ጊዮርጊሶች የመጨረሻ የማጥቃት አጋጣሚ ለመፍጠር እየጣሩ ነው።
90+2 የጅማ አባ ቡና ግብ ጠባቂ ሙላቱ አለማየው ሰዐት በማባከን የቢጫ ካርድ ተመልክቷል።
90′ ተጨማሪ ደቂቃ 5
89′ ታደለ ምህረቴ ሰዐት በማባከን ቢጫ ካርድ ታመልክቷል።
86′ አሁንም አሜ መሀመድ ከሳጥኑ ግማሽ ጨረቃ ላይ ያገኘውን ኳስ ሲሞክር ሳላዲን ባርጌቾ ተደርቦበታል። አጥቂው የሚያገኛቸውን አጋጣሚዎች ሁሉ ለመጠቀም እየሞከረ ይገኛል።
85′ አሜ መሀመድ በግምት ከ35 ሜትር በቀጥታ የሞከረውን ኳስ ፍሬው ወንድሙ በቀላሉ ይዞበታል።
83′ የጅማ አባ ቡናዎች የመከላከል መስመር ከመጀመሪያው ጋር ሲነፃፀር አሁን ሰፊ ክፍተት እየታየበት ነው። ቅዱስ ጊዮርጊሶችም ከፍተኛ ጥቃት እየሰነዘሩ ይገኛሉ።
80′ ራምኬል ሎክ ከግራ መስመር አክርሮ የመታው ኳስ በተከላካዮች ሲጨረፍ ከግቡ ጥቂት ሜትሮች ርቀት ላይ ሳልሀዲን ሰይድ በቮሊ ለማቆጠር ቢሞክርም ካስ ወደሰማይ ወጥታለች። የማይታመን አጋጣሚ !
78′ የተጨዋች ቅያሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ያስር ሙገርዋ ገብቶ ምንተስኖት አዳነ ወጥቷል።
77′ ካመሀል ሜዳ በጥቂቱ ቀርብ ብሎ የተሰጠውን ቅጣት ምት ሱራፌል አወል በቀጥታ መቶ ለጥቂት በግቡ አናት ወጥቶበታል።
75′ አሜ መሀመድ ከግብ ጠባቂው ጋር ያገናኘውን የመጨረሻ ኳስ ኪዳኔ አሰፋ አገባው ተብሎ ሲጠበቅ ወደውጪ ልኮታል።
72′ የተጨዋች ቅያሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ
አበባው ቡጣቆ በመሀሪ መና ተቀይሮ ገብቷል።
71′ አዳነ ግርማ ከቅርብ ርቀት የሞከረውን ኳስ ተከላካዮች ተደርበው አውጥተውበታል።
69′ ጎል !!! ቅዱስ ጊዮርጊስ ሳልሀዲን ሰይድ
ከማዕዝን ምት የታነሳውን ኳስ የጅማ ተከላካዮች በአግባቡ ማውጧት ተስኗቸው ሳልሀዲን የአቻነቷን ጎል አስቆጥሯል።
68′ የተጨዋች ቅያሪ ጅማ አባ ቡና
ክርስቶፈር ንታንቢ ወጥቶ ሀይደር ሸረፋ ገብቷል።
66′ ሳልሀዲን ሰይድ ከጅማዎች ሳጥን ጠርዝ ላይ በቮሊ የሞከረው ኳስ ወደላይ ወጥቷል።
65′ ክርስቶፈር ንታንቢ ከረጅም ርቀት የሞከረው ኳስ በ ፍሬው ወንድሙ ተይዞበታል።
65′ አዳነ ግርማ ከሳልሀዲን የተቀበለውን ኳስ ይዞ በጅማ አባ ቡና ተከላካዮች መሀል ይዞ ለምግባት ቢሞክርም ኳስ በቀላሉ በሙላት አለማየሁ ተይዛለች።
64′ ጅማዎች በቁጥር ብልጫ የተጋጣሚያቸው ሜዳ ላይ ቢገቡም ያገኙትን ጥሩ የመልሶ ማጥቃት አጋጣሚ ሳይጠቀሙበት ቀርተዋል።
61′ ጅማ አባ ቡናዎች በመልሶ ማጥቃት ጫና እየፈጠሩ ነው። የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች በሜዳው የተለያዩ ክፍሎች ብስጭታቸውን እየገለፁ ይገኛሉ።
59′ ሳልሀዲን ባርጌቾ መሀል ሜዳ ላይ በአሜ መሀምድ ላይ በሰራው ጥፋት ምክንያት የቢጫ ካርድ ተመልክቷል። አሜ ላይ በሰሩት ጥፋት ሁለቱም የቅዱስ ጊዮርጊስ የመሀል ተከላካዮች የቢጫ ካርድ ሰለባ ሆኑ ማለት ነው።
57′ የተጨዋች ቅያሪ ጅማ አባ ቡና
ዳዊት ተፈራ ገብቶ ቢንያም ኃይሌ ወጥቷል።
56′ የተጨዋች ቅያሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ
አዳነ ግርማ ገብቶ አቡበከር ሳኒ ወጥቷል።
54′ ናትናኤል ዘለቀ ከሳጥን ውጪ አክርሮ የሞከረውን ኳስ ግብ ጠባቂው አውጥቶበታል። ጨዋታውም በማዕዘን ምት ሲቀጥልም የተሻማውን ኳስ ሳልሀዲን ሰይድ ሞክሮ በግቡ አናት ወጥቶበታል።
50′ ጅማ አባ ቡናዎች አንደኛውን አጥቂ ሱራፌል አወልን ወደኋላ በመመለስ እና አሜ መሀመድን በብቸኛ አጥቂነት በመጠቀም መሀል ሜዳ ላይ በጥብቅ እየተከላከሉ ነው።
47′ ክርስቶፈር ንታንቢ ተጎድቻለው ብሎ ሲወድቅ ዳኛው ሰዐት ለመግደል ነው በሚል ቢጫ ካርድ አሳይተውታል። ከዚህ ጋር በተያያዘም ሳልሀዲን ሰይድም ከዳኛ ጋር በመኳሟገቱ ሌላ ቢጫ ካርድ ተመልክቷል።
46′ የተጨዋች ቅያሪ ጅማ አባ ቡና
ቴውድሮስ ገ/ፃዲቅ መጥቶ ሀይለየሱስ ብርሀኑ ገብቷል።
ሁለተኛው አጋማሽ በቅዱስ ጊዮርጊሶች አማካይነት ተጀምሯል።
የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰልጣኛች እና ተጨዋቾች ወደመልበሻ ክፍል ሲገቡ ከፍተኛ ተቃውሞ ከግራ ጥላ ፎቅ ደጋፊዎች ገጥሟቸዋል።
የመጀመሪያው ግማሽ በ ጅማ አባ ቡና 1-0 መሪነት ተጠናቀቀ
45+2 ሳልሀዲን ሰይድ ከግራ መስመር ያሻማውን ኳስ ግብጠባቂው ይዞታል።
45′ ተጨማሪ ደቂቃ 3
43′ ከጎሉ መቆጠር በኋላም የጊዮርጊሶች የኳስ ቁጥጥር የእንግዳዎቹን የአማካይ ክፍል ማለፍ ተስኖታል። ደጋፊውም ተቃውሞውን ቀጥሏል።
42′ መሀል ሜዳ ላይ ደጉ ደበበ በአሜ መሀመድ ላይ በሰራው ጥፋት የመጀመሪያውን የቢጫ ካርድ ተመልክቷል።
36′ ጎል !!! ጅማ አባ ቡና ኪዳኔ አሰፋ
ኪዳኔ በግምት ከ18 ሜትር በቀጥታ የመታትን ኳስ ፍሬው ቢጨርፋትም ማዳን ሳይችል ቀርቶ የጅማዎች የመጀመሪያ ጎል ሆናለች።
34′ አስቻለው ታመነ ከቀኝ መስመር ወደመሀል ገባ ብሎ ከጅማዎች ሳጥን ውጪ የሞከረውን ኳስ ሙላት በቀላሉ ይዞበታል።
31′ ከመሀል ሜዳ የተላከለትን ረጅም ኳስ ሱራፌል አወል ሲጨርፍለት አሁንም አሜ መሀመድ ከ ቅዱስ ጊዮርጊሶች ፍፁም ቅጣት ምት ክልል ውስጥ ገብቶ በቀጥታ ቢሞክርም ፍሬው ወንድሙ በድጋሜ ይዞበታል
25′ በመጀመሪያዎቹ ደቂቃዎች ላይ ይታዩ የነበሩ ሙከራዎች አሁን ላይ ተቀዛቅዘዋል። ጨዋታውም በመሀል ሜዳ ላይ በሚደጋገሙ ጉሽሚያዎች ቀጥሏል።
20′ ጨዋታው ወደ ጅማ አባ ቡና ሜዳ ክልል አድልቶ በፈረሰኞቹ የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ቀጥሏል። ጅማዎችም አልፎ አልፎ በመልሶ ማጥቃት ወደተጋጣሚያቸው ሜዳ ክልል ለመግባት እየጣሩ ይገኛሉ።
15′ አስቻለው ታመነ ከቀኝ መስመር ያሻማውን ኳስ ግብ ጠባቂው ሙላት አለማየው ለመያዝ ሲሞክር ስህተት ቢሰራም በአቅራቢያው የነበሩ ተከላካዮች አውጥተውታል ።
13′ አሜ መሀመድ ከመሀል ሜዳ የተላከላትን ኳስ ይዞ በመግባት ግብ ጠባቂውን ፍሬውን ካለፈ በኋላ ወደ ውጪ ሰዶታል።
10′ ቴውድሮስ ገ/ፃዲቅ ከሳጥን ውጪ የሞከረው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል።
9′ አሜ መሀመድ በግራ መስመር ይዞ የገባውን ኳስ ቢሞክርም ፍሬው ወንድሙ አድኖበታል።
6′ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች በካታንጋ በኩል የክቡር ይድነቃቸውን ዘመን እንናፍቃለን Martin Nooji out የሚል ባነር እያሳዩ ነው ። በግራ ጥላፎቅ በኩል ያሉ ደጋፊዎችም Martin Nooji out እያሉ ይገኛሉ።
1′ ጨዋታው ተጀምሯል ።
የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰላለፍ
1 ፍሬው ጌታሁን
15 አስቻለው ታመነ – 13 ሳልሀዲን ባርጌቾ– 12 ደጉ ደበበ – 3 መሀሪ መና
23 ምንተስኖት አዳነ – 26 ናትናኤል ዘለቀ – 27 አብዱልከሪም ኒኪማ
10 ራምኬል ሎክ – 7 ሳልሀዲን ሰይድ – 18 አቡበከር ሳኒ
ተጠባባቂዎች
22 ዘሪሁን ታደለ
2 ፍሬዘር ካሳ
4 አበባው ቡታቆ
20 ዘካርያስ ቱጂ
24 ያስር ሙገርዋ
25 አንዳርጋቸው ይላቅ
19 አዳነ ግርማ
የጅማ አባ ቡና አሰላለፍ
22 ሙላት አለማየሁ
6 ታደለ ምህረቴ– 21 በኃይሉ በለጠ – 19 ልደቱ ጌታቸው – 5 ጀሚል ያዕቆብ
15 ቴውድሮስ ገ/ፃዲቅ – 27 ክርቶፈር ንታንቢ – 17 ቢንያም ሀይሌ – 16 ኪዳኔ አሰፋ
9 አሜ መሀመድ – 8 ሱራፌል አወል
ተጠባባቂዎች
1 በሽር ደሊል
18 ኃይለየሱስ ብርሃኑ
10 ቴዎድሮስ ታደሰ
14 ሂድር ሙስጠፋ
11 ዳዊት ተፈራ
4 ሄይደር ሸረፋ
ኪሩቤል ተካ
09፡50 ተጨዋቾቹ ወደመልበሻ ክፍል ገብተዋል። በመቀጠል የሁለቱን ቡድኖች አሰላለፍ ይዘን እንመለሳለን።
09፡45 ጨዋታው እስኪጀምር ድረስ የሁለቱን ቡድኖች ደረጃ ለማስታወስ ያህል ቅዱስ ጊዮርጊስ በ 21 ነጥቦች በሊጉ 3ተኛ ደረጃ ላይ እንዲሁም ተጋጣሚው ጅማ አባ ቡና በ9 ነጥቦች 14ተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።
የእለቱን ተጋጣሚዎች የመጨረሻ ሶስት ውጤቶች ብንመለከት ቅዱስ ጊዮርጊስ በ9ኛው እና በ10ኛው ሳምንት አዲስ አበባ ስታድየም ላይ ድሬደዋ ከተማን እና ወልድያ ከተማን 3 -0 እና 1-0 ሲረታ በ11ኛው ሳምንት ላይ ወደ ሀዋሳ ተጉዞ ከሀዋሳ ከተማ ጋር በ 1 – 1 ውጤት መለያየቱ ይታወሳል።
ጅማ አባ ቡና በበኩሉ 9ኛው ሳምንት ላይ ሲዳማ ቡናን በሜዳው 2 – 0 ሲረታ በመጨረሻዎቹ ሁለት ጨዋታዎች ግን ሶዶ ላይ በወላይታ ድቻ እንዲሁም በሜዳው በኢትዮጵያ ቡና በተመሳሳይ 1 – 0 ውጤት ተሸንፏል።
09 ፡ 36 የሁለቱ ቡድኖች ተጨዋቾች ሰውነታቸውን እያሟሟቁ ይገኛሉ ።
ሠላም እንደምን ውላችኋል ውድ አንባቢዎቻችን ። በ12ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጨረሻ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጅማ አባ ቡናን በአዲስ አበባ ስታድየም ሲያስተናግድ እንደተለመደው ሶከር ኢትዮጵያ በቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት የጨዋታውን ዋና ዋና ክንውኖች የምታስነብባችሁ ይሆናል ።
መልካም ቆይታ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር!