ጎራን ስቴቫኖቪች የዋልያዎቹ አሰልጣኝ ሊሆኑ ተቃርበዋል

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አሰልጣኝ ጎራን ስቴቫኖቪች ቀጣዩ የብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ለመሆን መቃረባቸውን አስታወቀ፡፡

የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ጁይነዲ በሻ ዛሬ ጠዋት ከኤፍ ኤም አዲስ ጋር ባደረጉት የቀጥታ ስልክ ቃለ-ምልልስ ፌዴሬሽኑ ሰርቢያዊውን አሰልጣኝ ለመሾም እንደወሰነ ተናግረዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ እነደተናገሩት አሁን የቀረው የአሰልጣኙ ወደ አዲስ አበባ መምጣት እና በደሞዝ ጥቅማጥቅሞችና በሌሎች ቅድመ ሁኔታዎች ላይ ድርድር ማድረግ ብቻ ነው፡፡

አቶ ጁይነዲ ጨምረው እንደገለፁት የሰርብያዊው አሰልጣኝ ምክትሎች እና የአሰልጣኞች ስታፍ አወቃቀር ላይ ፌዴሬሽኑ በጎራን ስቴቫኖቪች ላይ ጣልቃ የማይገባ ሲሆን የአሰልጣኙን ውሳኔም ያከብራል፡፡ ነገር ግን በፌዴሬሽኑ ውስጥ ያለው ሀሳብ የአሰልጣኝ ስታፉ በኢትዮጵያውያን እንዲዋቀርና የሀረጋችን ባለሙያዎች ልምድ እንዲቀስሙ ማድረግ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ፌዴሬሽኑ ባለፈው ሳምንት ፖርቱጋላዊው ማርያኖ ባሬቶን አሰልጣኝ አድርጎ ለመሾም መወሰኑን ባስታወቀ በጥቂት ቀናት ውስጥ ከጎራን ስቴቫኖቪች ጋር የተቋረጠው ድርድር በድጋሚ በመቀጠሉ ውሳኔውን መቀልበሱ ይታወሳል፡፡

{jcomments on}

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *